ኢህአዴግ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች
ረቡዕ፣ የካቲት 8 2009ማስታወቂያ
ሁለተኛው የኢህአዲግ እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ውይይት ዛሬ ተካሂዷል ። በዛሬው ውይይት ከየፓርቲዎቹ የቀረቡትን ሃሳቦች ጨምቆ የድርድር እና የውይይት ሰነድ የሚያዘጋጅ ኮሚቴ ተሰይሟል ። በውይይቱ የተካፈሉት ፓርቲዎች ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በቅድመ ድርድር ሂደት መካተት አለባቸው ያሏቸውን ሃሳቦች በዛሬው ውይይት ላይ አቅርበዋል ። ሁለቱ ወገኖች ዛሬ የተመረጠው ኮሚቴ በሚያዘጋጀው ሰነድ ላይ ለመወያየት እና ሰነዱንም ለማጽደቅ ለዛሬ ሳምንት ሐሙስ ቀጠሮ ይዘዋል ። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ