የአፍንጫ መድማት ወይም ነስር
ማክሰኞ፣ መጋቢት 6 2008ማስታወቂያ
ነስር ድንገተኛ እና አስደንጋጭ የመሆኑን ያህል አብዛኛዉን ጊዜ ቤት ዉስጥ ሊቆጣጠሩት የሚቻል እንደሆነ አንዳንድ የህክምና ጽሑፎች ይጠቁማሉ። ሆኖም አልፎ አልፎ ደግሞ ብዙ ደም የሚፈስበት ከባድ ነስር ሲያጋጥም የሀኪም ርዳታ ማግኘት አማራጭ እንደማይኖረዉም ያሳስባሉ። የአፍንጫ መድማት ወይም ነስር መንስኤዉ አንድ ብቻ አይደለም፤ የተለያዩ ህመሞች እና ምክንያቶች ሊያመጡት እንደሚችሉ ዶክተር ቶሌራ ወልደየስ የዉስጥ ደዌ ከፍተኛ ሃኪም አስረድተዋል። መንስኤዎቹ የሚጣሩት ችግሩ ያጋጠመዉ ግለሰብ ሃኪም ጋር ቀርቦ በሚደረግ ምርመራ እና ማብራሪያ አማካኝነት ነዉ። እንደሃኪሙ ከሆነ ነስሩ ከፍተኛ ሲሆን ብቻ አይደለም ወደሃኪም መሄድ የሚገባዉ። የሚነስረዉ ሰዉ መንስኤዉን ለማወቅ ከአንገት በላይ ህክምና ባለሙያ ዘንድ ሄዶ በምን ምክንያት ያ እንደተከሰተ መመርመር ይኖርበታል። ነስር በሽታ ነዉ? አንድ ሰዉ ሲነስረዉ በመጀመሪያስ ምን ማድረግ ይኖርበታል? የሃኪሙን ማብራሪያ እና ምክር ለመከታተል የድምጽ ዘገባዉን ይጫኑ።
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ