1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ግጭትና ምክንያቶቹ

ሐሙስ፣ ሰኔ 18 2007

ጥናት ላይ የሚካፈሉት ምሑራን እንደሚሉት አፍሪቃ ዉስጥ ግጭቶችን ለማቀጣጠል እንደምክንያት የሚጠቀሱት በርካታ ጉዳዮች ናቸዉ።ግጭቶቹን ለማስወገድ በአብዛኛዉ የሚወሰደዉ ዕርምጃ ግን አንድ-ቢበዛ ሁለት ነዉ።ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ።ሁለቱ ሰዎች አንደሚሉት ለየግጭቶቹ ዘላቂ መፍትሔ ለማስገኘት ግን ሌሎች አማራጮችም መካተት አለባቸዉ።

https://p.dw.com/p/1Fmjj
ምስል Elenathewise/Fotolia

[No title]

በተለያዩ የአፍሪቃ ሐገራት የተቀሰቀሱ ግጭቶችን ለማስወገድ ከወታደራዊዉ እርምጃ ይልቅ በምጣኔ ሐብታዊ፤ማሕበራዊና አካባቢያዊ መፍትሔ ላይ ቢተኮር ዘላቂ ዉጤት ሊገኝ እንደሚችል ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ ምሕራን መከሩ።መንበሩን ካናዳ ያደረገ አንድ ተቋም ሥለ አፍሪቃ ግጭቶች መንስኤና መፍትሔዎቻቸዉ በሚያደርገዉ ጥናት ላይ የሚካፈሉት ምሑራን እንደሚሉት አፍሪቃ ዉስጥ ግጭቶችን ለማቀጣጠል እንደምክንያት የሚጠቀሱት በርካታ ጉዳዮች ናቸዉ።ግጭቶቹን ለማስወገድ በአብዛኛዉ የሚወሰደዉ ዕርምጃ ግን አንድ-ቢበዛ ሁለት ነዉ።ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ።ሁለቱ ሰዎች አንደሚሉት ለየግጭቶቹ ዘላቂ መፍትሔ ለማስገኘት ግን ሌሎች አማራጮችም መካተት አለባቸዉ።የዋሽግተኑ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ