የአፍሪቃ የመሪዎች ጉባኤና መፈክሩ
ረቡዕ፣ ጥር 19 2002ማስታወቂያ
የአፍሪቃ ሕብረት አባል ሐገራት የመሪዎች ጉባኤ የፊታችን እሁድ አዲስ አበባ ዉስጥ ይጀመራል። የዘንድሮዉ ጉባኤ በተለያዩ የአፍሪቃ ሐገራት ሠላም ለማስፈን የሚደረገዉ ጥረት ሥለሚጠናከርበት ሁኔታ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።የሕብንረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳት ዣን ፒንግ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንዳስታወቁት የመጀመሪያ ወሩን ያገባደደዉ የጎርጎሮሳዉያኑ ሁለት ሺሕ አስር ዓመት የአፍሪቃ የተሐድሶ፥ የሠላምና ደሕንነት አመት ተብሎም ተሰይሟልም።ታደሰ እንግዳዉ ከዚያዉ ከአዲስ አበባ ዝር ዝሩን ልኮልናል።
ታደሰ እንግዳው/ነጋሽ መሐመድ/ተክሌ የኋላ