የወጣት መሪዎች ጉባኤ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 26 2008ማስታወቂያ
አፍሪቃውያን ወጣት «መሪዎች» የተባሉት የአህጉሪቱ ወጣቶች የተሳተፉበት ጉባኤ ትናንት በዋሽንግተን ዲሲ ተጀመረ ። በዚሁ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ49 የአፍሪቃ ሃገራት የተውጣጡ ወደ 1 ሺህ የሚጠጉ ወጣቶች እና የአሜሪካን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል ። 51 ወጣት ኢትዮጵያውን በተካፈሉበት በዚህ ጉባኤ መክፈቻ ላይ እንደሚገኙ ተነግሮ የቀሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በመዝጊያው ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።ጉባኤው ላይ የተገኙት ወጣቶች ላለፉት 6 ሳምንታት የተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ዩኒቨርስቲዎችን ጎብኝተዋል። የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ አለው ።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ