የአፍሪቃ ኅብረት እና የአውሮጳ ኅብረት ስብሰባ
ዓርብ፣ ኅዳር 8 2010ማስታወቂያ
የአፍሪቃ ኅብረት እና የአውሮጳ ኅብረት በሠላም እና በጸጥታ ጉዳዮች ላይ የጀመሩትን የጋራ ሥራ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ስምምነት ላይ ደርሰዋል። የአፍሪቃ ኅብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት ከአውሮጳ ኅብረት የፖለቲካ እና ደህንነት ኮሚቴ ጋር በጋራ በሚያከናው 10ኛው የምክክር ጉባኤ ላይ የስደተኞች ጉዳይና በግጭት የፈረሱ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ማቋቋም ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶታል። በአፍሪቃ ኅብረት አዳራሽ ትናንት የጀመረው ውይይት የሚጠናቀቀው በነገው እለት ነው። የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ጉባኤውን ተከታትሎ ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅሮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ