1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ስደተኞች አስተዋፅኦ በአሜሪካ

ዓርብ፣ ጥቅምት 26 2008

የአፍሪካ ስደተኞቹ ከሌሎች ሀገራት ስደተኞች ጋር ሲነፃፀሩ የተማሩ ቢሆንም የተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ግን ከችሎታቸው በታች ስለሆነ በአሜሪካ ኢኮኖሚ ውስጥ የጎላ ሚና የላቸውም።ያም ሆኖ ከአጠቃላዩ የዩስ አሜሪካ ህዝብ የጎሳ ስብጥር አንጻር የአፍሪካውያን ስደተኞቹ ቁጥር ዝቅተኛ የሚባል እንደሆነም የጥናት ማእከሉ አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/1H158
Obama Sieg Wahlnacht an der Howard University
ምስል DW

በአሜሪካን ማህበራዊ ጉዳዮች በህዝብ አስተያየቶች እና በህዝብ ቆጠራ ላይ ያተኮሩ ጥናቶችን የሚያካሂደው ፒው የጥናት ማእከል የተባለው ተቋም ከጎርጎሮሳዊው 1970 ጀምሮ በአሜሪካ የሰፈሩ የአፍሪቃ ስደተኞች ቁጥር እያደገ መምጣቱን በቅርቡ ይፋ ባደረገው ጥናቱ ላይ አስታውቋል። እንደ ጥናት ተቋሙ መረጃ ከሆነ በ1970፣80ሺ ብቻ የነበሩት የአፍሪቃ ስደተኞች በአሁኑ ሰዓት ቁጥራቸው ከ1.8 ሚሊዮን ልቋል። ለአፍሪቃውያን ስደተኞች ወደ አሜሪካ መፍለስ ዋነኛ ምክንያት የተባለው ግጭትና ጦርነት ነው። የአፍሪካ ስደተኞቹ ከሌሎች ሀገራት ስደተኞች ጋር ሲነፃፀሩ የተማሩ ቢሆንም የተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ግን ከችሎታቸው በታች ስለሆነ በአሜሪካ ኢኮኖሚ ውስጥ የጎላ ሚና የላቸውም።ያም ሆኖ ከአጠቃላዩ የዩስ አሜሪካ ህዝብ የጎሳ ስብጥር አንጻር የአፍሪካውያን ስደተኞቹ ቁጥር ዝቅተኛ የሚባል እንደሆነም የጥናት ማእከሉ አስታውቋል። ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ዘጋቢያችን ናትናኤል ወልዴ የአፍሪካ ስድተኞች በአሜሪካ ኢኮኖሚ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን አስተዋጻኦ በተመለከተ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ናትናኤል ወልዴ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ