1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ሰላምና መረጋጋት ባለፉት 50 ዓመታት

እሑድ፣ ግንቦት 25 2005

የአፍሪቃ አገራት ሙሉ በሙሉ ከቅኝ ገዥዎችና ከነጭ ዘረኞች አገዛዝና ጭቆና መላቀቃቸውና አፍሪቃውያንም መቀራረባቸው ትልቁ የ 50 ዓመት ፍሬ ቢሆንም በአንፃሩ ድርጅቱ የአፍሪቃውያንን መብቶችና መሠረታዊ ነፃነቶች አለማስጠበቁ በዋነኛ ድክመትነት ይነሳል ።

https://p.dw.com/p/18i6y
ምስል picture alliance/ZUMAPRESS.com

ባለፈው ሳምንት በፊት 50 አመቱን ያከበረው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪቃ ህብረት ከተመሰረተባቸው ዓላማዎች ውስጥ የአፍሪቃ አገራትን ሉዓላዊነት ፣ የግዛት አንድነትና ነፃነት ማስጠበቅ የአፍሪቃውያንን አንድነትና ትብብርን ማጠናከር ፣ ለተሻለ ህይወት ማብቃት ይገኙበታል ። የአፍሪቃ አገራት ሙሉ በሙሉ ከቅኝ ገዥዎችና ከነጭ ዘረኞች አገዛዝና ጭቆና መላቀቃቸውና አፍሪቃውያንም መቀራረባቸው ትልቁ የ 50 ዓመት ፍሬ ቢሆንም በአንፃሩ ድርጅቱ የአፍሪቃውያንን መብቶችና መሠረታዊ ነፃነቶች አለማስጠበቁ በዋነኛ ድክመትነት ይነሳል ። በአንዳንድ የአህጉሪቱ ክፍሎች እስካሁን ሰላምና መረጋጋት ማስፈን አለመቻሉም ከህብረቱ ዋነኛ ችግሮች ይደመራል ። በዚህ ረገድ ኮንጎ ሱዳን ሶማሊያ ሊቢያ ማሊ ና ሌሎች ሃገሮችም ተጠቃሽ ናቸው ። ባለፉት 50 ዓመታት የአፍሪቃ ሰላምና መረጋጋት እንዴት ይገመገማል ? ችግሮቹ ምን ነበሩ ? መፍትሄውስ ምንድነው ? 3 እንግዶችን አወያይተናል ሙሉ ውይይቱን እንድታዳምጡ እንጋብዛለን

ሂሩት መለሰ

ልደት አበበ

መስፍን መኮንን

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ