1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ምጣኔ ሐብትና ጀርመን

ረቡዕ፣ ግንቦት 1 2004

ከግንቦት አስራ-ሰወስት ጀምሮ ላንድ ሳምንት የሚቆየዉ «የአፍሪቃ የንግድ ሳምንት» የአፍሪቃና የጀርመንን የምጣኔ ሐብት ሽርክና ለማጠናከር ጠቃሚ ነዉ።ጀርመን ከደቡብ አፍሪቃ በስተቀር ከሠሐራ-በስተደቡብ ከሚገኙት የአፍሪቃ ሐገራት ጋር ያላት የንግድ ልዉዉጥ ደካማ ነዉ

https://p.dw.com/p/14sLt
Bundeskanzlerin Angela Merkel (CDU) spricht am Mittwoch (17.06.2009) auf einem Afrika-Kongress der CDU/CSU-Bundestagsfraktion im Bundestag in Berlin. Unter dem Motto «Afrika und Deutschland - Nachhaltige Partnerschaft auf Augenhöhe» debattierten Politiker und Experten. Foto: Tim Brakemeier dpa/lbn +++(c) dpa - Report+++
ምስል picture-alliance/dpa

09 05 12


የአፍሪቃ መሪዎች፥ የኩባንያ ባለቤቶች፥ ነጋዴዎችና የሲቢል ማሕበረሰብ ተጠሪዎች ሥለ አፍሪቃ ምጣኔ ሐብት እድገት አዲስ አበባ ዉስጥ እየተነጋገሩ ነዉ።ከአስር ቀን በኋላ ደግሞ የጀርመኗ የንግድ ማዕቀል ፍራንክፈርት፥ «የአፍሪቃ የንግድ ሳምንት» የተባለዉን ስብሰባ ታስተናግዳለች።በፍራንክፈርቱ ስብሰባ የአፍሪቃና የአዉሮጳ የምጣኔ ሐብት አዋቂዎች፥ የንግድና የኩባንያ ተቋማት ተጠሪዎች ይካፈላሉ።በየሥፍራዉ የሚደረገዉ ጉባኤና ስብሰባ የአፍሪቃን ምጣኔ ሐብት ለማሳደግ የሚኖረዉ ፋይዳ እያነጋገረ ነዉ።የዶቸ ቬለዉ ባልደረባ ቶማስ ሞሽ እንዘገበዉ ግን በተለይ የፍራክፈርቱ ሥብሰባ የአፍሪቃና የጀርመንን የንግድ ሽርክና ለማጠናከር መርዳቱ አይቀርም።ነጋሽ መሐመድ ዝር ዝሩን አሰባስቦታል።

አዲስ አበባ የፈረንሳዩ ዜና ወኪል አዣንስ ፍራንስ ፕረስ እንደዘገበዉ በሰባት መቶ እንግዶች ተጨናንቃለች።የሥምንት ሐገራት መሪዎች፥የብዙ ሐገራት ሚንስትሮች፥ የዓለም የምጣኔ ሐብት መድረክ ባለሥልጣናት፥ የኩባንያ ባለቤቶችና ባለሙያዎች ለታደሙበት ጉባኤ የሚወጣዉ ገንዘብ ለአፍሪቃዊዉ ቢታደል-የስንት ጉሮሮ በደፈነ-ነበር?-ማሰኞ አልቀረም።

የብዙዎቹ ጉባኤተኞች መልስ እንደ ብዙዉ ጉባኤ ሁሉ ይኸኛዉም ለአፍሪቃዊያን ዶሆች ፍቱን-መፍትሔ ሰጪነቱን እንደሚጠቁሙ ለማወቅ ጉባኤተኞቹ እስኪናገሩ መጠበቅ አያስፈልግም ። ከኢትዮጵያ-እስከ ናይጄሪያ፥ ከጅቡቲ እስከ ጋቦን የሚገኙ የአፍሪቃ መሪዎች የተሳተፉበት ጉባኤ ለአፍሪቃ ልማትና እድገት እነሱ እንደሚሉት ፍቱን መፍትሔ ጠቁሞ በተጠናቀቀ በሳምንቱ ግድም ከአዲስ አበባዎቹ ጉባኤተኞች ገሚሱ ወደ ፍራንክፈርት ያቀናሉ።

ሌላ ሥብሰባ። ሌላ ወጪ። ሌላ መፍትሔ።ቶማስ ሞሽ እንደዘገበዉ ግን ከግንቦት አስራ-ሰወስት ጀምሮ ላንድ ሳምንት የሚቆየዉ «የአፍሪቃ የንግድ ሳምንት» የአፍሪቃና የጀርመንን የምጣኔ ሐብት ሽርክና ለማጠናከር ጠቃሚ ነዉ።ጀርመን ከደቡብ አፍሪቃ በስተቀር ከሠሐራ-በስተደቡብ ከሚገኙት የአፍሪቃ ሐገራት ጋር ያላት የንግድ ልዉዉጥ ደካማ ነዉ።የድክመቱ ሰበብ አፍሪቃ ዉስጥ የሚሰሩ የጀርመን ኩባንዮች ማሕበር ሊቀመንበር ሽቴፋን ሊቢንግ እንደሚሉት አፍሪቃዉያን የጀርመንን ሸቀጥ ሥለማይፈልጉ አይደለም።ዋጋቸዉ-እንጂ፥

«በመላዉ አፍሪቃ የሚሰማዉ ለጀርመን ምርትና ለቴክኖሎጂዉ ጥራት ከፍተኛ ዋጋ እንደሚሰጠዉ ነዉ።የዚያኑ ያሕል ግን የጀርመን ሸቀጦች ዉድ ናቸዉ።ላጭር ጊዜ ትንሽ ገንዘብ ያለዉ ቅናሽ ዋጋ ያለዉን ሸቀጥ ለመግዛት ይወስናል።»

በመቶኛ ሲሰላ የጀርመን የዉጪ ንግድ ወደ አፍሪቃ የሚልከዉ ሸቀጥ በጣም ትንሽ ነዉ።ያም ሆኖ ሰባት መቶ የጀርመን ኩባንያዎች ምርታቸዉን ወደ አፍሪቃ መላካቸዉ አልቀረም። ባሁኑ ወቅት ቻይናን የመሰለ ታላቅ ተፎካካሪ የገጠማቸዉ የጀርመን ኩባንዮች ሁነኛ ብልሐት ካልፈለጉ እስካሁን ችላ ያሉት የአፍሪቃ ገበያ፥ ከእንግዲሕ ችላ የሚላቸዉ ገበያዉ ራሱ ነዉ።ይሕ እንዳይሆን ሊቢንግ እንደሚያምኑት ኩባንዮቹ አዲስ ሥልት መቀየስ አለባቸዉ።

«እኔ እንደሚመስለኝ የጀርመን ኩባንዮች በጣም የተራቀቁና ከፍተኛ ደረጃ የደረሱትን ሸቀጦች ብቻ ሳይሆን መጠነኛ እድገት ያላቸዉ ሐገራትን አቅም የሚመጥን አይነት ሸቀጥ ማምረት ይኖርባቸዋል።»

አፍሪቃዉን ከጀርመን የሚሹት አቅማቸዉን የሚመጥን ሸቀጥ ብቻ አይደለም።እንዲያዉም ዋጋ ከመቀስ ይልቅ የጀርመን እዉቀትና ቴክኖሎጂ ወደየሐራቸዉ የሚተላለፍበትን የንግድ ልዉዉጥ ይሻሉ።በተለይ ባሁኑ ወቅት የሐይል ምንጭ ቴክኖሎጂ ፍላጎቱ አፍሪቃ ዉስጥ በጣም ከፍተኛ ነዉ።

በቅርቡ ጀርመንን የጎበኙት የናጄሪያዉ የሳይንስና የምርምር ጉዳይ ሚንስትር ኢታ ኦኮ-ባሴይ ኢዋ እንዳሉትም የጉብኝታቸዉ ዋና አላማ ይኸዉ ነበር።

«በዚሕ ረገድ በተለይ ከሽቱትጋርት ዩኒቨርስቲ ጋር ግንኙነት ካላቸዉ የጀርመን ድርጅቶች ጋር ወዳጅነት ለመመሥረት ሞክረናል።ይሕ በእኔ እንደማምነዉ የናጄሪያ አቻዎቻቸዉ እዚሕ መጥተዉ ሥለ የፀሐይ ሙቀትን ወደ ኤሌክትሪክ ሐይል ሥለሚቀይረዉ ቴክኖሎጂ ይማራሉ»

እንደ ናይጄሪያ ሁሉ ጋና እና እንጎላን የመሳሰሉ ሐገራትም የሐይል ምንጭን ጨምሮ ሌሎች ጥሬ አላባዎቻቸዉን ጥቅም ላይ ወደሚዉል ሸቀጥ መለዉጥ የሚችሉበትን እዉቀትና ቴክኖሎጂን ማዳበር ይሻሉ።ጀርመን ለመጀመሪያ ጊዜ የምታስተናግደዉ የፍራንክፈርቱ የአፍሪቃ የንግድ ሳምንትም የአፍሪቃዉያንን ፍላጎት ከአዉሮጳ በጣሙን ከጀርመናዉያኑ አቅርቦት ለማጣጣም ይረዳል ነዉ-እምነቱ።

Afrika Baumwollernte außen , Mann , Arbeit , photograph , Republic of Zimbabwe , Chisumbanje , Land , Auswirkung , Männer , Sammeln , Getreide , Tag , Leute , Afrikanisch , Farbe , im Freien , Baby , Afrika , Frau , David Reed , Erwachsener , Baumwolle , Fotographie , landwirtschaftlich , Landwirtschaft , Rhodesien , draußen , horizontal , Frauen , ImpactPhotos1 , Kerl , Ernte , Tragen , Gruppe Leute , Funktion , Betrieb , Zimbabwe , Ernten , Dame , Bewirtschaften
የአፍሪቃ ጥጥምስል picture-alliance/David Reed/Impact Photos

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ