1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ምሁራንና ቅኝ አገዛዝ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 28 2005

በተከታታይ የሚፅፉና አስተያየት የሚሠጡት አፍሪቃዉያን ምሁራን እንደሚሉት የቀድሞ አዉሮጳዉያን ቅኝ ገዢዎች ተመልሰዉ አፍሪቃን ቢገዙ የአሕጉሪቱን ሕዝብ በራሱ ወገኖች አሁን ከሚያየዉ ስቃይ ይገላግሉታል

https://p.dw.com/p/19baS
. Women in Kyengeza fetch water at a borehole
የአፍሪቃ ሴቶችምስል Leylah Ndinda

አንዳድ የአፍሪቃ ምሁራንና ታዋቂ ሠዎች አፍሪቃ አሁን ካለችበት ፖለቲካዊ አገዛዝ ይልቅ በነጭ ቅኝ ገዢዎች ትገዛ በነበረበት ወቅት ሕዝቧ የተሻለ ሠላም፥ ፍትሕና ምጣኔ ሐብታዊ ጥቅም ያገኝ እንደነበር እየተናገሩ፥ እየፃፉም ነዉ።ትምሮንጋ ክሮኒክል በተሰኘዉ የአፍሪቃ ጉዳይ መፅሔት በተከታታይ የሚፅፉና አስተያየት የሚሠጡት አፍሪቃዉያን ምሁራን እንደሚሉት የቀድሞ አዉሮጳዉያን ቅኝ ገዢዎች ተመልሰዉ አፍሪቃን ቢገዙ የአሕጉሪቱን ሕዝብ በራሱ ወገኖች አሁን ከሚያየዉ ስቃይ ይገላግሉታል።የአፍሪቃ ጉዳይ የፖለቲካ አጥኚዎች እንደሚሉት ግን አፍሪቃዉያኑ ምሑራን የቀድሞ ቅኝ ገዢዎችን እስከ መጋበዝ የደረሱት አሁን ያሉት የአፍሪቃ መሪዎች የሚያደርሱን ግፍ ለማሳየት እንጂ በርግጥ ቅኝ ገዢዎችን ናፍቀዉ ሊሆን አይችልም።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል አጭር ዘገባ አለዉ።

ይልማ ሐይለሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ