1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ እና የሶማሊያ ሰላም

ሰኞ፣ ጥር 21 1999

ዛሬ አዲስ አበባ የተሰየመዉ የአፍሪቃ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በሶማሊያ ዘላቂ ሠላም ለማስፈን እስካሁን የተደረገዉን ጥረት ገምግሞ ይወስናል ተብሎ ይጠበቃል።

https://p.dw.com/p/E0Yq
የአፍሪቃ ህብረት ባንዲራ
የአፍሪቃ ህብረት ባንዲራምስል AP

በጉባኤዉ ከሚካፈሉት ሐገራት አንዳዶቹ የሶማሊያን ሠላም ለማስከበር ሊዘምት ለታቀደዉ የአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት ወታር ለማዋጣት ፍቃደኞች መሆናቸዉ እየተነገረ ነዉ።ይሁንና በዚሑ ጉባኤ የሚካፈሉት የኢጣሊያዉ ጠቅላይ ሚንስትር እና በአፍሪቃ ሕብረት የዩናይትድ ስቴትስዋ አምባሳደር እንደሚሉት በሶማሊያ ዘላቂ ሠላም የሚሰፍነዉ ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ ወገኖች በሙሉ ሲደራደሩ ብቻ ነዉ።ነጋሽ መሐመድ ዝር ዝሩን አጠናቅሮታል።