የአፍሪቃ ሕብረትና ግብፅ
ሐሙስ፣ ሰኔ 12 2006ማስታወቂያ
መቆየቱ የሚታወስ ነው። ሕብረቱ፤ በተለይም የሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ኮሚሽኑ ፤ ከትናንት በስቲያ ፣ ማክሰኞ ማታ በሰፊው ከተወያየ በኋላ፣ ትናንት መልሶ ተቀብሏታል። ጊኒ ቢሳዎንም መልሶ ተቀብሏል ። እልባት ያላገኘው የማዕከላዊት አፍሪቃ ሪፓብሊክ ጉዳይ ብቻ ነው። የአፍሪቃ ደንብ ፤ የአባል ሃገራት ፣ መንግሥታት በዴሞክራሲ የተመረጡ መሆን አላባቸው ይላል። በክፍለ ዓለሙ በጣት በሚቆጠሩት እጅግ ጥቂት ሃገራት በስተቀር ፤ በብዙዎቹ ዓለም አቀፍ መሥፈርትን በሚገባ ያሟላ ምርጫ ሲካሄድ አልታየም። የግብጽን ወደ አፍሪቃ ሕብረት መመለስ በተመለከተ ፤ ተክሌ የኋላ ፤ የአፍሪቃውን ቀንድ የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ አቶ ዩሱፍ ያሲንን በስልክ አነጋግሯቸዋል።
ተክሌ የኋላ
ኂሩት መለሰ