1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃው ቀንድና የ«ኬር ኢንተርናሽናል« የእርዳታ ጥሪ፧

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 9 2000

በኬንያ ሶማልያና ኢትዮጵያ በምግብ ዋጋ መናር፧ ባልተቋረጠ ድርቅና ግጭት ሳቢያ፧ 14 ሚልዮን ህዝብ ለብርቱ ረሀብ እንደሚጋለጥ፧ Care International የተሰኘው ዓለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት አስጠነቀቀ።

https://p.dw.com/p/E0Yz
ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ሶማልያውያን ተረጂዎች፧
ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ሶማልያውያን ተረጂዎች፧ምስል AP

በመሆኑም እርዳታ እንዲደርስ ማሳሰቢያ አቅርቧል። በኬንያ መዲና በናይሮቢ ተቀማጭ የሆኑትን የድርጅቱ የምሥራቅና የማዕከላዊ አፍሪቃ ዋና ሥራ አስኪያጅ፧ Steve Wallace...... ።
የአፍሪቃው ቀንድ ኣካባቢ አገሮች፧ በደን መራቆት፧ በአየር ጠባይ መዛባት፧ በሰው ሠራሽ ችግሮችም ሳቢያ፧ ህዝባቸው፧ የእርዳታ እህል ተመጽዋች ከሆነ አያሌ ዓማታትን አስቆጠረ። አሁን ደግሞ«ኬር ኢንተርናሽናል« የተሰኘው ዓለም አቀፍ የግብረ ሠናይ ድርጅት የማስጠንቀቂያ ደወል እያሰማ ነው። ስለችግሩ አሳሳቢነት Mr. Steve Wallace...
«አዎ፧ አሳሳቢ የሆነ ድርቅ በአፍሪቃው ቀንድ በተለይ በሶማልያ.፧ ኬንያና ኢትዮጵያ ገብቷል። ለጊዜው፧ በአጭር ጊዜ የፈጥኖ ደራሽ፧ የእርዳታ ተገባራችን፧ ሶማልያ ውስጥ 600,000 ያህል ህዝብ በመመገብ ላይ ነን። ከሰኔ ጀምሮ ንን ቁጥራቸው 800,000 መድረሱ አይቀርም። የዝናሙ መጠን፧ ከሶማልያ ይልቅ በኬንያና ኢትዮጵያ ከጣለው የተሻለ ነበር። ስለሆነም፧ የአስቸኳይ ሁኔታው እርዳታ እዚያ ይበልጥ ተፈላጊ ነው። CARE፧ በኬንያ፧ ድርቅ እጅግ ወዳጠቃቸው አካባቢዎች ውሃ በማቅረብ፧ ኢትዮጵያም ውስጥ፧ ለቀንድ ከብቶች መኖ በማቅረብ፧ ለማኅበረሰባት የውሃ ማጣረቃሚያ በመስጠት፧ እንዲሁም ለተጎሳቆሉ ልጆች ምግብ በማደል ሥራውን ያከናውናል።«
ረሀብ ሲያስጨንቅ፧ የሚሰጠው ነፍስ-አድን እርዳታ፧ አስፈላጊነቱ ባያጠራጥርም፧ ለዘለቄታው የሚበጅ መርኀ-ግብር ተዘርግቶ ባለመሠራቱ፧ ረሀብን መቋቋም እንዳዳገተ ነው። የ«ኬር« የረጅም ጊዜ እቅድ ምን ይመስላል?
«የረጅም ጊዜ አቅድን በተመለከተ፧ CARE ታላላቆቹ የእርዳታ ማኅበረ-ሰባት፧ አሁኑኑ ተጨባጭ እርምጃ ቢወስዱ አግባብ ያለው እንደሚሆን እርምጃቸውም፧ ችግር ከመከሠቱ በፊት፧ አስቀድሞ በመከላከል ላይልንዲያተኩር ያደርጉ ዘንድ ይመክራል። አብዛኛውን ጊዜ ብዙ እንጠብቃለን።እርዳታውም እጅግ ዘግይቶ ነው የሚደርሰው። ስለዚህ፧ እርምጃ መውሰጃ ጊዜው አሁን ነው። ሁኔታው እጅግ እየተባባሰ ስለሚሄድ አሁን፧ ምግብ ማደል ተገቢ ይሆናል።
Mr. Steve Wallace ለድርቅኣነሀብ፧ ተጨማሪ የሚያብብሱ ሁኔታዎች መከሠታቸውን አንዱም፧ የምግብ ዋጋ መናር መሆኑን ጠቁመዋል። የነዳጅ ዘይት ዋጋ ማሻቀብ፧ በቆሎ የነዳጅ ዘይትን ቦታ እንዲተካ መጠየቁ፧ የምግብ ፍጆታ ይዞታና የመሳሰለውም በዓለም ዙሪያ የምግብን ዋጋ መናር እንዳስከተለ፧ በተለይ በዚህ ሂደት እጅግ የደኸዩት አገሮች ኑዋሪዎች መሠቃየታቸውንም አያይዘው አስረድተዋል። በ 1990 ኛዎቹ ዓመታት ያየነው የአየር ንብረት ለውጥ አስከፊ እየሆነ መምጣቱን ለመገንዘብ ነው የቻልን። ምንም እንኳ፧ ድርቅና ረሀብን ለመቋቋም ጥረት ቢደረግም፧ ችግሩ ይበልጥ እየከፋ በመሄዱ፧ እንደ እኣስቲቭ ዋለስ ገለጻ፧ ጥረቶችን ሁሉ መቅኖ ያሳጣቸዋል። ለመሆኑ ውዝግቦች፧ ግጭቶች፧ ድርቅንና ረሀብን መቋቋም እንዳይቻል፧ ስለሚፈጥሩት ደንቃራ «ኬር« የቱን ያህል ተከታትሏል?
«ውዝግብ፧ ድርቅን ለመቋቋም፧ የሚደረግ ጥረትን የሚገታ ሳንክ ነው። በተለይ በሶማልያ፧ በይበልጥም በምዕራብ ወሰኖች በኩል! መውጫ-መግቢያ ማግኘት ያዳግታል። አሳሳቢ የሆነ፧ ሰዎችን አፍኖ የመውሰድ እርምጃ ይከናወናል። ወደ ቦታው እንዳንደርስየሚሊሺያ ጦረኞች እንቅሥቃሴ ደንቃራ ሆኖብናል። እርዳታ እጅግ የሚያስፈልጋቸንው ሰዎች ፈልገን ለማግኘትና ለመርዳታ እንደተቸገርን ነን! የተፈናቀሉ ሰዎች ፍልሰት አለ። በዚያ፧ ሠራተች ቢኖሩንም እንኳ፧ በህይወታቸው ላይ አሥጊ ሁኔታ እንደተደቀነባቸው ነው የሚገኙት። ሶማልያ፧ ኬንያና ኢትዮጵያ በሚዋሰኑበት አካባቢ፧ ችግሩን በጥሞና መርምሮ ለመንቀሳቀስ፧ ችግሩን ጠንቅቆ ካወቁ በኋላም ለመርዳት፧ በጣም ከባድ ነው። አስተማማኝ የፀጥታ ዋስትና የለምና!።«