1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃውያን ስደተኞች የተቃውሞ ሰልፍ በእሥራኤል

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 28 2006

በሺ የሚቆጠሩ አፍሪቃውያን ስደተኞች ፤ እሥራኤል ውስጥ መብታቸው እንዲከበር ትናንት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል ፤ እንዲሁም ዛሬ ቴል አቪብ ውስጥ

https://p.dw.com/p/1Am3x
Afrikanische Flüchtlinge demonstrieren in Israel
ምስል Reuters

ከምዕራባውያን ኤምባሲዎች ፊት ለፊት በመሰለፍ ፣ እሥራኤል ፤ ባወጣቸው አዲስ ህግ በረሃ ውስጥ ይዛ ያሠረቻቸው ባልደረቦቻቸው እንዲፈቱላቸው ያደርጉ ዘንድ መጠየቃቸው ተመልክቷል ። በአሥራኤል ባጠቃላይ ፤ 60 ሺ ያህል አፍሪቃውያን ስደተኞች እንደሚገኙ ይነገራል። እሥራኤል እነዚህን ሰዎች ህገ ወጥ ሥራ ፈላጊዎች ናቸው ትላለች፤ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ደግሞ ስደተኞች መሆናቸውን ነው የሚገልጹት። ስደተኞቹ ትናንት ስላካሄዱት ሰልፍ ዓለማ ፤ ከሃይፋ ፣ እሥራኤል፣ የዶቸ ቨለ ዘጋቢ ግርማው አሻግሬ የሚከተለውን ልኮልናል።

ግርማው አሻግሬ

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ