1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃዉ ህብረት እና ሊቢያ

ሰኞ፣ ነሐሴ 23 2003

ባለፈዉ ሳምንት አርብ በሊቢያ ጉዳይ ላይ አቋም ለመያዝ የተሰበሰበዉ የአፍሪቃዉ ህብረት ለሊቢያ የሽግግር ምክር ቤት እዉቅና ለመስጠት ተቸግሮ ታይቶአል።

https://p.dw.com/p/RiiH
የደቡብ አፍሪቃዉ ፕሪዝደንት ጃኮብ ዙማምስል AP

በአንድ በኩል አንዳንድ የአፍሪቃ አገራት በሊቢያ የሚቋቋመዉ የሽግግር መንግስት የጋዳፊን ወገኖችንም ያካተተ መሆን አለበት ሲሉ በሌላ በኩል እንደ ኢትዮጽያ ናይጀርያ ሩዋንዳ የመሳሰሉ አገሮች ከስብሰባዉ ዋዜማ ጀምሮ ለሊቢያዉ የሽግግር ምክርቤት እዉቅና በመስጠታቸዉ በህብረቱ ልዪነት ተፈጥሮአል። ስብሰባዉን የመሩት የደቡብ አፍሪቃዉ ፕሪዝደንት ጃኮብ ዙማ ለሊቢያዉ የሽግግር ምክር ቤት እዉቅና እንዳይሰጥ በጥብቅ ሲከራከሩም ታይቶአል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ፕሪዝደንት ጃኮብ ዙማን አነጋግሮ ዘገባ ልኮልናል።

ታደሰ እንግዳዉ

አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ