የአፋር መድረክ ጉባኤ
ዓርብ፣ ነሐሴ 25 2004ማስታወቂያ
የአፋር የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመብት ተከራካሪ ድርጅቶች እንዲሁም በኢትዮጵያ በተለይም በአፋር ህዝቦች የፖለቲካና ኤኮኖሚያዊ ሁኔታ ላይ ጥናት ያካሄዱ ምሁራን የተካፈሉበት ጉባኤ ብራሰልስ ቤልጂግ ውስጥ ትንናት ተጀምሯል ። በ 2 አመት አንዴ የሚካሄደውን ይህኑኑ ጉባኤ ያዘጋጀው የአፋር መድረክ የተባለው ድርጅት ነው ። በአንድነት ለሰላምና እድገት በሚል መርህ በተዘጋጀው በዚሁ ጉባኤ ላይ በቤልጅየምና አካባቢው የሚኖሩ የአፋር ተወላጆች የአውሮፓ ህብረት ባለሥልጣናትና የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል ። ስብሰባው የሥራ እቅዶችንና በማፅደቅና ውሳኔዎችን በማሳለፍ እሁድ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ። ገበያው ንጉሴ ከብራሰልስ ዝርዝሩን ልኮልናል
ገበያው ንጉሴ ፣
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ