የአፈር ለምነት ጥናት በኢትዮጵያ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 26 2008ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ በዓይነቱ የተለየ የአፈር ለምነት ጥናት ማካሄዷን መረጃዎች ያመለክታሉ። እንዲህ ያለዉ ጥናት በአፍሪቃ ሲካሄድም ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ መሆኗም ተገልጿል። በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸዉ የዘርፉ ባለሙያ እንደሚሉት ከሆነም ከመላዉ ዓለምም ቢሆን ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ ብዙዎች ይህን ጥናት ለማካሄድ አልደፈሩም። በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡን የዘርፉ ባለሙያ ፕሮፌሰር ተካልኝ ማሞ አገራዊ የአፈር ለምነት ዳሰሳ ጥናት መርሃ ግብር ኃላፊ ናቸዉ። ፕሮፌሰሩ ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት ኢትዮጵያ ላለፉት አራት ዓመታት በ495 ወረዳዎች አገራዊ የአፈር ለምነት ዳሰሳ ጥናት አካሂዳለች። በዚህ የዳሰሳ ጥናትም በየአካባቢዉ የሚገኘዉ አፈር የትኛዉ ንጥረ ነገር እንደጎደለዉ ለመገንዘብ ተችሏል። ጥናቱ የሰብል ምርትና ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ እና እያሽቆለቆለ የመጣዉን የአፈር ለምነት ይዞታም ለማሻሻል ያለመ ነዉ። የዳሰሳ ጥናቱ ምን ምንን አካቷል? በምግብ እጥረት ችግር ለሚጎዳዉ ወገንስ የሚያመጣዉ ፋይዳ ምን ይሆን? ዝርዝሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያገኙታል።
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ