1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አባበ ቀላል የባቡር ፕሮጀክት

ዓርብ፣ መጋቢት 12 2006

ኮርፖሬሽኑ በከተማዋ በመገንባት ላይ ባሉት ሁለት መስመሮች ማለትም በሰሜን ደቡብ ና በምስራቅ ምዕራብ መስመሮች በቀን ወደ 250 ሺህ መንገደኞች ለማጓጓዝ አስቧል ።

https://p.dw.com/p/1BU0w
Addis Abeba
ምስል picture alliance / landov

የአዲስ አበባው ቀላል የባቡር ትራንስፖርት ፕሮጀክት በሚቀጥለው ዓመት የሙከራ ሥራውን እንደሚጀምር የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ ። የኮርፖሬሽኑ የኦፐሬሽንና አገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ከ10 ወራት በኋላ ሥራው ተጠናቆ የቀላል ባቡር ትራንስፖርት የሙከራ አግልግሎት ይጀመራል ። ኮርፖሬሽኑ በከተማዋ በመገንባት ላይ ባሉት ሁለት መስመሮች ማለትም በሰሜን ደቡብ ና በምስራቅ ምዕራብ መስመሮች በቀን ወደ 250 ሺህ መንገደኞች ለማጓጓዝ አስቧል ። ህብረተሰቡንም ሊከሰቱ ከሚችሉ አደጋዎች ለመጠበቅ ግንዛቤ የማስጨበጥ እቅድ አለ ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ