1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ የቅየሳ ማሻሻያና የኑዋሪዎች ስሞታ፣

ማክሰኞ፣ ኅዳር 4 2005

Lonley Planet የተሰኘ ለቱሪስቶች ዓለም አቀፍ ጉዞ-ነክ አገልግሎት ሰጪና መረጃ አቅራቢ ኩባንያ፣ ከ 2 ሳምንት ገደማ በፊት ባወጣው መግለጫ ላይ ፣ አዲስ አበባን ፣ ከአፍሪቃ በአንደኝነት ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃም 9ኛ ላይ በማስቀመጥ

https://p.dw.com/p/16ijN

፣ ዘንድሮ ፤ በ ተለይም ታኅሳስ 23 ቀን 2005 በሚያብተው 2013 አዲሱ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ፣ ሊጎበኙ የሚችሉ እጅግ አርኪ ካላቸው ከተሞች መካከል መድቧታል። ሠናይ ዜና ነው። አገር ጎብኝዎችን የምታማልለው ከተማ ታዲያ በአንዳንድ ክፍለ ከተማዎች ለሚገኙ ኑዋሪዎቿ እንዴት የማትስማማበት ሁኔታ ይኖራል!?

አዲስ አበባ፤ እንደስሟ ሁሌም አዲስ ናት። 125 ዓመት ዕድሜ ቢኖራትም! አዳዲስ ህንጻዎች ይገነባሉ። ጠባብ መንገዶች እንዲሠፉ ይደረጋል። ይህ ሲሆን ግን፤ ምናልባት ሊጠበቅ የሚገባው ቅርስ አንዳንድ ወገኖች እንደሚሉት እንዲፈርስ እየተደረገ ነው ። በመሠረቱ፣ በአቅድ ያልተከተመን ከተማ አቅድ ማስያዝ አዲስ እንደመገንባት ቀላል ላይሆን ይችላል።

አንድ ጊዜ የተከተመበትን ቦታ እንዴት አድርጎ ነው ዘመናዊ አቅድ ማስያዝ የሚቻለው?

ለረጅም ጊዜ በአንድ ሠፈር የኖሩ ሰዎች፤ ቦታውን እንዲለቁ ሲደረግ ለዜጎቹ ደኅንነት ኑሮና ማኅበራዊ አገልግሎት አስቀድሞ እስከምን ድረስ ነው የሚታሰበው? የሚፈናቀሉ ሰዎችስ ተገቢውን ካሣ ያገኛሉ ወይ?የከተማ አቅድና የኗሪዎች ችግር የዛሬው ውይይታችን ርእስ ነው። በዚህ ርእስ ላይ ለመወያየት 3 እንግዶችን ጋብዘናል ።

እነርሱም፣

1,በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ፣ የቅየሳ፣ ንድፍ የማውጣት ባለሙያ የሆኑት አቶ ማቴዎስ አስፋው በቀለ፣ --

2, በምህንድስና የታወቁት ኢንጂኔር ኃይሉ ሻውል

3, በአዲስ አባባ ሲቭል ምህንድስና (ሲቭልኢንጂኔሪንግ )የተማሩትና አሁን ድሬዳዋ ውስጥ በሥራ ላይ የሚገኙት አቶ እንዳለ ሽኩር ናቸው።

ተክሌ የኋላ

መሥፍን መኮንን