የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት
የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ትራንስፖርት ከመስከረም 9 ጀምሮ በአንድ መስመር አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ።
ዘመናዊው የአዲስ አበባ ከተማ ባቡር
የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ትራንስፖርት ከመስከረም ዘጠኝ 2008 ዓ ም ጀምሮ በአንድ መስመር አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ። አንዳንድ የባቡሩ ተሳፋሪዎች በተጀመረው አገልግሎት ደስታ ተሰምቷቸዋል።
የከተማ ባቡር መንገደኞች
ባቡሩ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ጊዜ አንስቶ ተሳፋሪዎች ተሰልፈው ተራ ሲጠብቁ ተስተውለዋል።
አዲስ አማራጭ የመጓጓዧ አገልግሎት
የቀላል ባቡሩ አገልግሎት በመዲናዋ እስከ 60 000 መንገደኞችን በቀን የማመላለስ አቅም አለው። ይህም የከተማይቱን የመጓጓዣ ዘዴ እጥረትን ያቃልላል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል ።
የቲኬት መቁረጫ
ተሳፋሪዎች ለቲኬት መቁረጫ በተዘጋጁ መሸጫዎች ቲኬታቸውን ይገዛሉ።የቲኬቱ ዋጋ እንደ መንገዱ ርዝመት ከሁለት ብር እስከ ስድስት ብር ነው።
ጎዞ በባቡር
ለበርካታ ተሳፋሪዎች በቀላል ባቡር መጓጓዝ አዲስ እና ያልተለመደ ተሞክሮ ነው።
ግንባታ
ለዚህ ፕሮጀክት 475 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገ ሲሆን ከዚህም 85 ከመቶ ያህሉን ብድር የሰጠው Exim የተባለው የቻይና ባንክ ነው።
ወደ ባቡሩ የሚያደርሱት ደረጃዎች
ለጊዜው በአገልግሎቱ እየተጠቀሙ ያሉት ደረጃ የመውጣት እና የመውረድ አቅም ያላቸው ሰዎች ብቻ ናቸው። አንዳንድ አካል ጉዳተኞች እና አዛውንቶች እስካሁን የዚህ ውጤት ተጠቃሚ መሆን አልቻሉም። ይህ ችግር ኤስኬሌተሩ( በኤሌክትሪክ የሚሰራው ደረጃ) አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ሊቃለል እንደሚችል ይታመናል።
ደንብ አለማክበር
በቀላል ባቡሩ ተጠቃሚዎች ዘንድ በተለያዩ አጋጣሚዎች በማወቅ እና ባለማወቅ የደንብ አለማክበር ስህተት ሲፈፀም ይታያል።
የዋሻ ፌርማታ
የዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ ፌርማታ በዋሻ ውስጥ የሚገኝ ፌርማታ ነው።