የአዲስ አበባ አዲስ የታክሲ ስምሪትና ችግሩ
ረቡዕ፣ ግንቦት 3 2003ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ለታክሲዎች አዲስ ያወጣዉ የቀጠና ስምሪት ወትሮም በማመላለሻ እጥረት የሚቸገረዉን የከተማይቱን ነዋሪ ለከፋ ችግር ዳርጎት ነዉ የዋለዉ።ዛሬ ገቢራዊ የሆነዉ አዲስ ሕግ ታኪሲዎች ከተመደበላቸዉ መነሻና መድረሻ ዉጪ መንገደኛ ማመላለስ አይችሉም።አዲሱ ሕግ በተወሰኑ አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ የታክሲ እጥረት ሲያስከትል፥ በሎች አካባቢዎች ደግሞ ታኪሲዎች ያለ ተሳፋሪ ባዷቸዉን እንዲጓዙ አስገድዷቸዋል።ታደሰ እንግዳዉ መንገደኞችንና ባለታክሲዎችን አነጋግሮ ነበር።
ታደሰ እንግዳዉ
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ