የአዲስ አበባ ቀላል የባቡር ጉዞ ሙከራ
እሑድ፣ ጥር 24 2007ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር እሁድ ጥር 24 ቀን፤ 2007 ዓም ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና ሌሎች ባለሥልጣናት በተገኙበት የሙከራ ጉዞ ማድረጉን የአዲስ አበባው ወኪላችን በላከልን ዘገባ ጠቅሷል። የሙከራ ጉዞው ቢያንስ ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት ማለትም የወርሃ ሚያዝያ ማብቂያ እና የግንቦት ወር መጀመሪያ ድረስ እንደሚቆይም ተገልጧል። የሙከራ ጉዞው ደኅንነቱ አስተማማኝ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ይሆናል ተብሏል። ሙሉ ዘገባውን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር እንደሚከተለው ያቀርበዋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ