1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ ማስፋፊያ አቅድና የተማሪዎች ተቃዉሞ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 24 2006

ኦሮሚያ መስተዳደር በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች ፤ የኦሮሞ ብሔር አባላት የሆኑ ተማሪዎች ፣ የኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ፣ ከኦሮሚያ ክልል ቦታ በመጨመር የምትሰፋበትን አካሄድ በሰላማዊ ተቃውሞ ሲገልፁ፤ ከፖሊስ ጋ በተፈጠረዉ ግጭት ቢያንስ 11 መገደላቸውን መንግስትን ጠቅሶ አሶሲየትድ ፕረስ ከአዲስ አበባ ዘግቧል።

https://p.dw.com/p/1Bt2F
Addis Abeba
ምስል picture alliance / landov

በዚህ ሳምንት መግቢያ ላይ የተጀመረው ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆን፤ የክልሉ ፖሊስ የተማሪዎቹ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ በፀረ መንግስት ኃይሎች ሳይጠለፍ አይቀርም ሲል ባወጣዉ መግለጫ መጥቀሱንም ዘገባዉ አመልክቷል። እንደዘገባዉም ቢያንስ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች የተቃዉሞ ሰልፉ የተካሄደ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ዩኒቨርሲቲዉ ወዳለበት ከተማም ተስፋፍቷል። መንግሥት ፀረ ሰላም ባላቸው በነዚህ ኃይሎች አመፅ 70 ሰዎች መቁሰላቸውም ተገልጿል ። ሆን ተብለው የተነዙ አሳሳች ባላቸው ወሪዎችና ሃሜቶች ግራ የተጋቡ ተማሪዎች በዚህ ሳምንት የጀመሩት ረብሻ በቁጥጥር ስር መዋሉንም መንግስት ትናንት ማታ ባወጣው መግለጫ መንግስት አስታውቋል ።ከረብሻው በስተጀርባ አንዳንድ ፀረ ሰላም ያላቸው ኃይሎች እንዳሉበት ፖሊስ ባወጣው መግለጫ ኣስታውቋል ። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የኦሮሞ ፌደራል ኮንግረስ ዋና ፀሃፊ አቶ በቀለ ናዳ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተካሄደው ተቃውሞ ሰላማዊ ቢሆንም በአምቦ ዩኒቨርስቲ ግን ፖሊስ በወሰደው የኃይል እርምጃ የሰው ህይወት ሊጠፋ መቻሉን ገልፀዋል ።ስለተፈጠረዉ ችግር መንስዔና መፍትኄውም የኦሮሞ ፌደራል ኮንግረስ ምን ዓይነት ሐሳብ እንዳለው ፣ ተክሌ የኋላ ፤ የፓርቲውንም ሆነ ምክር ቤቱን ዋና ፀሐፊ አቶ በቀለ ናዳን በስልክ አነጋግሯቸዋል።

12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ