1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ ሙስሊሞች ዉሎ

ዓርብ፣ ኅዳር 7 2005

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መንግሥት ሐይማኖታዊ ነፃነታችንን ገፎናል በማለት በተለያዩ አካባቢዎች ተቃዉሟቸዉን ማሰማት ከጀመሩ ዓመት አልፏቸዋል።የኢትዮጵያ መንግሥት አመፅ ያነሳሳሉ ያላቸዉን የኮሚቴ አባላት ካሠረ ወዲሕ ደግሞ ተቃዉሞዉ ጠንከር ብሎ ነዉ የከረመዉ።

https://p.dw.com/p/16kik
Der Meskal Square im Zentrum der äthipischen Hauptstadt Addis Abeba von der großen Tribüne aus gesehen, links im Bild die kürzlich installierte Video-Wand. Aufnahme vom Januar 2007. Foto: Peter Smolka +++(c) dpa - Report+++
ምስል picture alliance/dpa

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የእርቅና መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ባለፈዉ ሐምሌ ከታሠሩ ወዲሕ የአዲስ አበባ ሙስሊሞች በየሳምንቱ አርብ ከስግደት በሕዋላ የሚያሰሙት ተቃዉሞ ዛሬ ጋብ ብሎ መዋሉን ዘጋቢያችን አስታዉቋል።የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መንግሥት ሐይማኖታዊ ነፃነታችንን ገፎናል በማለት በተለያዩ አካባቢዎች ተቃዉሟቸዉን ማሰማት ከጀመሩ ዓመት አልፏቸዋል።የኢትዮጵያ መንግሥት አመፅ ያነሳሳሉ ያላቸዉን የኮሚቴ አባላት ካሠረ ወዲሕ ደግሞ ተቃዉሞዉ ጠንከር ብሎ ነዉ የከረመዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር  እንዳስታወቀዉ ግን ለወትሮዉ የተቃዉሞ መልዕክት በሚሰማባቸዉ መስጊዶች ዛሬ የተለመደዉ ዓይነት ተቃዉሞ አልነበረም።ነጋሽ መሐመድ ዮሐንስን በስልክ አነጋግሮትል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ