የአዲስ አበባው ሰላማዊ ሰልፍ እና ወጣቱ
ዓርብ፣ ግንቦት 30 2005ማስታወቂያ
የኑሮ ውድነት፣ የወጣት ስራ አጥነት፣ ሙስና፣ በፀረ ሽብር ህግ ምክንያት የታሰሩ ፖለቲከኞች ና ጋዜጠኞች፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እንዲሁም የሙስሊሙ ህብረተሰብ ጥያቄ ፤ ባለፈው እሁድ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተነሱ ነጥቦች ናቸው። በዚህ ሰልፍ ላይ የተገኙ ሶስት ወጣቶች ከሰልፉ ምን ጠብቀው አደባባይ እንደወጡ ገልፀውልናል። ከዚህም ሌላየሰማያዊ ፓርቲ መስራች የስራ አስፈፃሚ አባልና የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ ሀና ዋለልኝ ለሰልፉ የማነቃቃት ስራ ተካፍላ ነበር። ምን ይመስል እንደነበር ገልፃልናለች። ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።
ልደት አበበ
ተክሌ የኋላ