የአዲስ አበባና የተለያዩ ከተሞች የሙስሊሞች ዉሎ
ዓርብ፣ ኅዳር 14 2005ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ የአንዋር መስጊድ በአርብ ስግደት ላይ የተገኙ ሙስሊሞች ዛሬም እንደ ሳምንቱ ተቃውሞ እንዳላሰሙ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን አስታውቋል ። ሆኖም ዘጋቢያችን እንዳለው ኢሉባቡር ውስጥ በአንድ መስጊድ ጠንካራ ተቃውሞ የተሰማ ሲሆን በጅማም ሙስሊሞች የታሰሩት ይፈቱ ሲሉ ጠይቀዋል ። ዛሬ በተለያዩ የኢትዮጲያ ከተሞች የሙስሊሞች ውሎ ምን ይመስል እንደነበር የአዲስ አበባውን ወኪላችንን ዮሐንስ ገብረን እግዚ አብሄርን ስቱድዮ ከመግባቱ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ