የ«አይ ኤስ» ግድያ እና የኢትዮጵያ አስተያየት12 ሚያዝያ 2007ሰኞ፣ ሚያዝያ 12 2007በሊቢያ እስላማዊ መንግሥት የተሰኘው አክራሪ ድርጅት 30 ኢትዮጵያውያንን በጥይትና በመቀላት የገደለበት የጭካኔ ተግባር ፣ እንዲሁም፣ በደቡብ አፍሪቃ በውጭ ዜጎች አንፃር በቀጠለው ሁከት በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው የኃይል ተግባር በኢትዮጵያ ተወገዘ።https://p.dw.com/p/1FBHqማስታወቂያ በደቡብ አፍሪቃው ሁከት አንድ ኢትዮጵያዊ ባለፈው ሳምንት በተጣለበት የቃጠሎ አደጋ ህይወቱ አልፋለች። የኢትዮጵያ መንግሥት: የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት እና የአፍሪቃ ሕብረት ኮሚሽን አረመኒያዊ እና ኢሰብዓዊ ሲሉ አውግዘውታል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከነገ ጀምሮ የሶስት ቀናት ብሔራዊ ሀዘን አውጆዋል። ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር አርያም ተክሌ ሂሩት መለሰ