1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአየር ጠባይ ለዉጥና አፍሪቃ

ማክሰኞ፣ መስከረም 12 2002

በአየር ጠባይ ለዉጥ ምክንያት በሚከተሉት የተፈጥሮ አደጋዎች ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸዉ ከሚገኙ የዓለማችን ክፍሎች ግንባር ቀደሟ አፍሪቃ መሆኗ ይነገራል።

https://p.dw.com/p/JmaA
...ደኗ የተራቆተዉ አፍሪቃ...ምስል picture-alliance/ dpa

ለአየር ጠባይ ለዉጥ አስተዋፅዖ ያደረጉትን አደገኛ ጋዞች ወደከባቢ አየር በመልቀቅ የበለፀጉት ሀገራት በተጠያቂነት ይወቀሳሉ። ለዚህም መዘዝ ለደረሰዉ ጉዳት አዳጊ ሀገራት ማካካሻና ድጋፍ ከሃብታሞቹ ይጠይቃሉ። በዚህ ረገድ አፍሪቃ ልቃ አቋሟን ከወዲሁ አሰምታለች። አንዳንዶች ተገቢነዉ ቢሉም በርካቶች ግን እያንዳንዱ የአፍሪቃ ሀገር ትርጉም ያለዉ የአካባቢ ጥበቃ ፖሊስና ያንን የማስፈፀም ተግባር ማከናወኑን ከጥያቄ ላይ ጥለዉታል። በሌላ ወገን የአየር ጠባይ ለዉጥ የሚያስከትለዉን ችግር ለመቋቋም ስልት ለመቀየስ ከሚደረገዉ ጥረት በጓዳኝ ለለቤተሰብ ምጣኔ አለመታሰቡ ስህተት ነዉ የሚሉ ወገኖች አሉ።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ