1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአየር በረራና ከውጭ የሚያጋጥሙት እክሎች፣

ረቡዕ፣ ጥር 20 2001

በየብስ ፣ አውቶሞቢሎችና ባቡሮች አደጋ በማያጋጥምበት ሁኔታ ይሽከረከሩ ዘንድ የትራፊክ ህግ መመሪያ ሆኖ እንደሚያገላግላቸው የታወቀ ነው። የንግድና የጦር መርከቦች ም ቢሆኑ በጭፍኑ አይደለም፣ በግዙፎቹ ውቅያኖሶች ላይ የሚቀዝፉት።

https://p.dw.com/p/Gi7S
ለአኤሮፕላን በራራ እንቅፋት የሚሆኑ አእዋፍ፣ምስል AP

በአየር ላይ የሚበሩ ጥያራዎችም በአገር አቀፍና ዓለም-አቀፍ መመሪያ ደንብ፣ በራዳር አማካኝነት መስመራቸውን (ከፍታንና ዝቅታን ይጨምራል)ጠብቀዉ ስለሚበሩ፣ በአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ወይም በአብራሪዎች ስህተት ካልተፈጠረ በስተቀር የግጭት አደጋ አያጋጥምም።