የአውሮፓ ፓርላማና የአፍሪቃ ቀንድ የሰብዓዊ መብት ይዞታ
ዓርብ፣ ጥር 15 2001ማስታወቂያ
በፈረንሣይ ከተማ በሽትራስቡርግ ተቀማጭ የሆነው ፓርላማው ባስተላለፈው ውሣኔ በነዚሁ ሃገራት ያለው የሰብዓዊ መብት ይዞታ እንዲሻሻል፣ ኤርትራና ኢትዮጵያ የድንበር ውዝግባቸውን በስምምነታቸው መሠረት ዕልባት እንዲያስይዙና ጂቡቲና ኤርትራም እንዲሁ ችግራቸውን በሰላም እንዲፈቱ አሳስቧል። የብራስልስ ወኪላችን ገበያው ንጉሤ የፓርላማውያን እንደራሴና የተልዕኮውን መሪ አላን ሃቺንሰንን በተለይም በኢትዮጵያ ጉዳይ አነጋግሮ ነበር፤ አጠናቅሮ የላከው ዘገባ የሚከተለው ነው