የአውሮፓ ፓርላማና የአርመኖች ጭፍጨፋ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 8 2007ማስታወቂያ
የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ኦቶማን ቱርክ በአርመናውያን ላይ የፈፀመው ጭፍጨፋ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው ሲል ትናንት በአብላጫ ድምፅ ያሳለፈው ውሳኔ አርመንን ሲያስደስት ቱርክን ደግሞ አስከፋ ። ፓርላማው በጉዳዩ ላይ ድምፅ ከሰጠ በኋላ የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ የአውሮፓ ፓርላማ ሌላ ታሪክ ለመፃፍ እየሞከረ ነው ሲል ወቅሷል ። ከውሳኔው በፊት የቱርክ ፕሬዝዳንት ታይፕ ኤርዶጋን ውሳኔውን ከቁም እንደማይቆጥሩት ተናግረው ነበር ። የአርመን መንግሥት ውሳኔውን አወድሶ እርምጃው በሁለቱ ሃገራት መካከል እርቀ ሰላም እንዲወርድ መንገድ ጠራጊ እንደሚሆንም አስታውቋል ። ቱርክ የዛሬ መቶ ዓመት ከአርመን ጋር በተካሄደው ውጊያ በርካታ አርመናውያን መገደላቸውን ታምናለች ። ሆኖም ያኔ የርስ በርስ ጦርነት እንጂ የዘር ማጥፋት ወንጀል አልተፈጸም ስትል ነው የምትከራከረው ። የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ