የአውሮፓ የኒዩክልየር ኃይል ማመንጫዎች እና እጣ ፈንታቸው
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 19 2008ማስታወቂያ
የዩክሬኑ የቸርኖቤል የኒዩክልየር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ፣አደጋ የደረሰበት 30ኛ ዓመት ትናንት ታስቧል ። ከቸርኖቤሉ ፍንዳታ በኋላ የኒዩክልየር ኃይል ማመንጫ ካላቸው ሃገራት አንዳንዶቹ ቀስ በቀስ ጣቢያዎቹን እየዘጉ ነው ። የተወሰኑት ደግሞ ከዚያን ወዲህ አዳዲስ የኃይል ማመንጫዎችን ከፍተዋል ። በአሁኑ ጊዜም በአውሮጳ 128 የኒዩክልየር ማመንጫ ጣቢያዎች ይገኛሉ ። አንዳንዶቹ እድሳት የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ወጪው ግን ከፍተኛ መሆኑ አሳስቧል ። ሥራቸውን ይቀጥሉ ቢባል ደግሞ ሊከተል የሚችለው አደጋ ያሰጋል ። የዛሬው ከኤኮኖሚው ዓለም ትኩረት ነው ። ይልማ ኃይለ ሚካኤል አጠናቅሮታል .
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ