የአውሮፓ ዜጎች ወአሜሪካ ለመሄድ 14 ዶላር ሊከፍሉ ነው
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 11 2002ማስታወቂያ
አሜሪካ 36 ሀገራት ተጠቃሚ የሆኑበትና የመግቢያ መረሃግብሯን በተመለከተ አዲስ መመሪያ ማውጣቷ ከአውሮፓ ህብረት ተቃውሞን አስከትሏል። ከዚህ በፊት ወደ አሜሪካ ለስራም ይሁን ለጉብኝት የሚሄዱ የ36 ቱ ሀገራት ዜጎች የሚጠየቁት ምንም ነገር የለም። ከ2008 ወዲህ የአሜሪካ የሀገር ውስጥ የደህንነት መስሪያ ቤት ከእነዚህ ሀገራት ወደአሜሪካ ለሚገቡ ዜጎች አንድ ቅጽ በማዘጋጀት እንዲሞሉ ማድረግ ጀምሯል። ከመጪው መስከረም ወር መጀመሪያ አንስቶ 14 ዶላር ክፍያ እንደሚጀመርም ተገልጿል። የአውሮፓ ህብረት አዲሱን አሰራር በተመለከተ ቅሬታውን አሰምቷል። የአውሮፓ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ማቲው ኒውማን አዲሱን አሰራር አየመረመርን ነው ብለዋል።
መሳይ መኮንን
ነጋሽ መሐመድ