1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ሕብረት መሪዎችና አጀንዳዎቻቸው

ዓርብ፣ ሰኔ 20 2006

የአውሮፓው ሕብረት መሪዎች ትናንት ከብራሰልስ 150 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው፣ ከአንድ መቶ ዓመት በፊት፣ በአንደኛው የዓለም ጦርነት አውድማነት በምትታወቀው ከግማሽ ሚሊዮን የማያንስ ሠራዊት ባለቀባትና ለመጀመሪያ ጊዜ መርዘኛ የሰናፍጭ ጋዝ ሰለባ

https://p.dw.com/p/1CRhb
ምስል Reuters

በሆነችው ከተማ በመሰብሰብ ፣ በጦርነቱ ያለቁትን በልዩ ሥነ ሥርዓት አስበዋቸዋል።ከዚያም ወደ ብራሰልስ ተመልሰው ዛሬ እስከ ምሽት ደረስ ፣ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል ባሏቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።ብሪታንያ ብትቃወመም፣ የቀድሞውን የላክሰምበርግ ጠ/ሚንስትር ዣን ክሎድ ዩንከርን የኮሚሽኑ አዲስ ተሿሚ ይሆኑ ዘንድ ሰይመዋል። አወዛጋቢውና ለዩክሬይን ቀውስ ሰበብ የሆነው የሕብረቱና የዩክሬይን ነጻ የንግድ ስምምነት በጉባዔው ፊት ተፈርሟል። ይህ የዩክሬኑን የፖለቲካ ፍጥጫ በማርገብ ፤ አገሪቱ አንድነቷን ጠብቃ እንድትቀጥል የሚረዳ የመሆን ያለመሆኑ ጉዳይም ማነጋገሩ አልቀረም ። የስደተኞች ጉዳይ ሌላው ዐቢይ ርእስ ነበር።

ገበያው ንጉሤ

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ