የአውሮፓ ህብረት የስደተኞች አቀባበል መርህ
ሐሙስ፣ መስከረም 18 2004ማስታወቂያ
ከሰሜን አፍሪቃ በጀልባ ወደ ኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ የሚጎርፉት ስደተኞችና ፣ የተጨናነቁት የማልታና የግሪክ የስደተኞች ማጎሪያ ማዕከላት ምስሎች ፣ የአውሮፓ የስደተኞች አቀባበል ደንብ እንደገና እንዲፈተሽ አውሮፓውያን እንዲያሳስቡ እያደረገ ነው ። እጎአ በ2012 መጀመሪያ ላይ አሁን የሚሰራበት የአውሮፓ የስደተኞች አቀባበል ህግ እንደገና ይመረመራል። ከዚያ በኃላ የሚሆነው ደግሞ ተጨማሪ ትግል የሚያስፈልገው እንደሆነ ነው የዴቼቬለው የሪቻርድ ፉክስ ዘገባ የሚያስረዳው ።
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ