የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች ልዩ ጉባኤ
ሐሙስ፣ መስከረም 13 2008ማስታወቂያ
በአውሮፓ የስደተኞች ቀውስ ላይ አትኩሮ ትናንት እስከ እኩለ ለሊት ድረስ የተነጋገረው የአውሮፓ ህብረት ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል ። ጉባኤው የተጠራው በችግሩ መንስኤ በህብረቱ አባል ሃገራት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት እና ልዩነት በማጥበብ ፣ ችግሩን በጋራ መፍታት የሚችሉባቸውን ስልቶች ለመፈለግ ነበር ። በዚህ የጋራ ችግር ላይ የመከሩት የ28 የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት መሪዎች በልዩ ጉባኤያቸው ላይ ስላነሷቸው ሃሳቦችና ስላሳለፏቸው ውሳኔዎች የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ ቀጣዩን አገባ ልኮልናል ።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ