የአውሮፓ ህብረት እርዳታ ለአሚሶም
ረቡዕ፣ መስከረም 16 2005ማስታወቂያ
የአውሮፓ ህብረት በሶማሊያ የአፍሪቃ ህብረት ሰላም አስከባሪ አሚሶምን ለማገዝ ተጨማሪ 82 ሚሊዮን ዩሮ ለመስጠት መወሰኑን ትናንት አስታውቋል ። ይኽው ተጨማሪ እርዳታ አሚሶም ተልዕኮውን በሙሉ አቅሙ እንዲወጣ የሚያግዝ መሆኑን የአውሮፓ ህብረት ገልጿል ። ፣ህብረቱ ተጨማሪ እርዳታ የሰጠው ሶማሊያ ዘላቂ ሰላም እንዲኖራትና እንድትረጋጋ በሚደረገው ጥረት ወሳኝ ሚና የሚጫወተው የአሚሶም የእስካሁኑ ተግባር አበረታች በመሆኑ ምክንያት ነው ሲሉ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኑነቶች ቢሮ ቃል አቀባይ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። የብራሰልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ አለው ።
ገበያው ንጉሴ
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ