የአውሮፓ ህብረት ና ዚምባብዌ
ረቡዕ፣ መጋቢት 18 2005ማስታወቂያ
የአውሮፓ ህብረት በዚምባብዌ ላይ ጥሎት የነበረውን የኤኮኖሚና የጉዞ እገዳ ከትናንት ጀምሮ በአብዛኛው ያነሳ መሆኑን የህብረቱ የውጭ ግንኙነት ሃላፊ ካትሪን አሽተን አስታውቀዋል ። ውሳኔው የተላለፈው በቅርቡ በዚምባብዌ የተካሄደው ህገ መንግሥታዊ ህዝበ ውሳኔ ሠላማዊና ተአማኒ መሆኑን ተክትሎ እንደሆነ ካትሪን አሽተን ያወጡት መግለጫ ያስረዳል ። በውሳኔው መሰረት በ81 ግለሰቦችና በ8 ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው የንግድና የጉዞ እገዳ ተነስቷል ። የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤን ጨምሮ 10 ግለሰቦችና 2 ኩባንያዎች ግን አህንም እገዳው እንደፀናባቸው ይቆያል ። ገበያው ንጉሴ ከብራስለስ ዝርዝር ዘገባ አለው ።
ገበያው ንጉሴ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ