የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች ቡድን ሀላፊ መግለጫ
ሰኞ፣ ግንቦት 9 2002ማስታወቂያ
ይኽው 60 አባላት ያሉት ቡድን በመላው የሐገሪቱ ክፍሎች 90 አባላት ያሉትን የህብረቱን የረዥም ጊዜ ቡድን እንደሚቀላቀል ህብረቱ አስታውቋል ። የታዛቢው ቡድን ሀላፊ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ ፣ ለአጭር ጊዜ ምርጫውን የሚታዘበው ቡድን አባላት ፣ ከዚህ ቀደም በሐገሪቱ ምርጫ ለመታዘብ እንደተሰማሩት የህብረቱ ታዛቢዎች የረዥም ጊዜ ልምድ ያላቸው እና ምርጫውንም በገለልተኝነት ለመታዘብ የሚያስችል ገለፃ የተሰጣቸው መሆኑን አስታውቀዋል ። ጋዜጣዊ መእግለጫውን የተከታተለው ታደሰ ዕንግዳው ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ታደሰ ዕንግዳው ፣ ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ