የአውሮፓ ህብረትና የአፍሪቃ አቀፍ የልማት እቅድ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 1 2006ማስታወቂያ
የአውሮፓ ህብረት ለአፍሪቃ አቀፍ የእድገት ትብብር የፓን አፍሪቃ መርሃ ግብር የመጀመሪያው ምዕራፍ 415 ሚሊዮን ዩሮ መመደቡን ትናንት አስታውቋል ። ይህ ገንዘብም ህብረቱ እጎአ እስከ 2020 ድረስ ለአፍሪቃ አቀፍ የልማት እቅድ ለመስጠት ከመደበው 845 ሚሊዮን ዩሮ ውስጥ የመጀመሪያው ልገሳ መሆኑ ነው ። ገንዘቡ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ እንደሚውል የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ትናንት አስታውቋል ። ባለፈው ሚያዚያ በተካሄደው የአፍሪቃና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች የጋራ ጉባኤ ላይ ነበር የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ሆዜ ማኑዌል ባሮሶ አፍሪቃ አቀፍ የልማት መርሃ ግብርን በይፋ ያበሰሩት ።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ