1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ህብረትና ሩስያ

ዓርብ፣ መጋቢት 12 2006

የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሩስያ ፣ በዩክሬን ስር የነበሩትን ክሪምያንና የሴቫስቶፖል ከተማን የፌደሬሽኗ አካል የምታደርግበትን ይፋ ሰነድ ዛሬ ፈርመዋል ።

https://p.dw.com/p/1BU2s
EU Gipfel in Brüssel (Unterzeichnung des Assoziierungsabkommens)
ምስል picture alliance/AP Images

ትናንትናና ዛሬ በክሪሚያ ሰበብ የምዕራቡ ዓለምናየሩስያ ውዝግብ ተካሯል የተካሄደው የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ሩስያ ክሪሚያን ወደ ግዛቷ ለመቀላቀል መወሰኗን በማውገዝ በ12 ተጨማሪ የሩስያ ባለስልጣናት ላይ የጉዞ እገዳ ጥሏል ፤ በውጭ የሚገኝ ሃብት ንብረታቸው እንዳይንቀሳቀስም አግዷል ። የሩስያ ምክር ቤት የክሪምያውን ህዝበ ውሳኔ ውጤት ተቀብሎ ክሪምያ ከሩስያ ጋር የምትቀላቀልበት ሂደት በተፋጠነበት ወቅት ላይ የተካሄደው የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጠንከር ያለውን የኤኮኖሚ ማዕቀብ ያስተላልፋል ተብሎ ነበር የተጠበቀው ። ጉባኤውን የተለታታለው የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ ዝርዝሩን ያቀርብልናል ።

ገበያው ንጉሴ

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ