የአውሮፓው ኅብረት 2 ዐበይት የምርምር ፕሮጀክቶች፤
ማክሰኞ፣ ጥር 28 2005ቅዝቃዜን መቋቋም ይችላል? አንድ የእስፖርትና የህክምና ባለሙያ የሚያካፍሉት ምክር አለ ።
በተለያዩ የሳይንስ ዘርፎች፣ ምርምር በማካሄድ ላይ ያሉ ጠበብት በየጊዜያቱ የማይናቁ ውጤቶችን ሲያስመዝግቡ መቆየታቸው እሙን ነው። በፊዚክስ ረገድ በርከት ካሉት የምርምር ውጤቶችና ግኝቶች በተጨማሪ፣ ባለፈው 2012 ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት በሃምሌ ወር፤ በፈረንሳይኛው አህጽሮት (CERN) በመባል የታወቀው የአውሮፓው የአቶም ምርምር ድርጅት ፣ የማንኛውም ቁስ አካል ምንጭ የሆነውን ኢምንት ቅንጣት «ሂግስ ቦሰን» ወይም «የእግዚአብሔር ቅንጣት» የተሰኘውን በምርምር ማግኘት መቻሉን አስታውቆ እንደነበረ አይዘነጋም። ተከሠተ የተባለው ኢምንት ቅንጣት ለአያሌ ዓመታት ይፈለግ የነበረው፤ በእስኮትላንዳዊው የፊዚክስ ሊቅ ፒትር ሂግስ ስም የሚጠቀሰው ሂግስ ቦሰን ወይም (ጎድስ ፓርቲክል) በትክክል ነው አይደለም? ዘንድሮ በሚካሄድ ቀጣይ ምርምር ተጣርቶ ሊታወቅ እንደሚችል ተስፋ ተደርጓል። ተስፋ የተጣለውም፤ ጀኔብ አጠገብ ፤ በእስዊትስዘርላንድና ፈረንሳይ ድንበር 27 ኪሎሜትር ገደማ 100 ሜትር ጥልቀት በትኅተ ምድር በተገነባው ቀለበት መሰል መሿለኪያ በተገነባው የምርምር ጣቢያ ፣ የአቶም ቅንጣቶችን በሚያጋጨው ግዙፍ መግነጢሳዊ መሣሪያ (ላርጅ ሃድሮን ኮላይደር ) ትብብር ነው።
የዚህ ምርምር ውጤት ፤ በተደጋጋሚ እንደተገለጠው፤ ከ 13,7 ቢሊዮን ዓመት በፊት ታላቁ የፍጥረተ ዓለም ፍንዳታ(Big Bang)ካጋጠመ በኋላ በሴኮንድ ቅጽበት ምን እንዳጋጠመ ፤ ማለትም ፍጥረተ ዓለም የተዘረጋበትን ሂደትም ሆነ ምሥጢር ለማወቅ ይረዳል ተብሎ ነው የሚታሰበው። የአውሮፓው ኅብረት አባል ሃገራት በኅብረተና በተናጠል በየዘርፉ ሰፊ የሳይንስ ምርምር ከማካሄድ አልቦዘኑም።--- የሩሲያ ግንባር ቀደም የኅዋ ምርምር ሳይዘነጋ ማለት ነው---። የአውሮፓው ኅብረት አሁንም ቢሆን ከሩሲያ ጋር በመተባበር ፣ በኅዋ ምርምር ረገድ ሰፊ እቅድ አለው።
በኢንዱስትሪ የበለጸጉት የአውሮፓ ሃገራት፣ ለኤኮኖሚ ዕድገታቸው ሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ሰፊ ድርሻ ማበርከቱን በመገንዘባቸውም ነው ፣ ለሳይንስ ምርምር ዓቢይ ግምት የሚሰጡት። ኅብረቱ ከትናንት በስቲያ በሰጠው መግለጫ መሠረት፣ ከ 26 ዋና- ዋና የምርምር ዓይነቶች መካከል ፣ ለመረጣቸው ሁለት የምርምር ፕሮጀክቶች፤ ከ 2 ቢሊዮን ዩውሮ በላይ ነው የተመደበው። ይህም ፕሮጀክቶቹ በሚመጡት 10 ዓመታት የምርምር ትልማቸውን መድፈን ያስችላቸው ዘንድ ገንዘቡን ሥራ ላይ ያውላሉ። የአውሮፓው ኅብረት ኮሚሽን፤ ምክትል ፕሬዚዳንት፤ ኔሊ ክሩስ ፣ በመግለጫቸው ላይ
እንዳስገነዘቡት፣ «አውሮፓ የዕውቀት ኅያል ማዕከል ሆና የመቀጠሏ ነገር የሚመረኮዘው፤ የማይታሰበውን በማሰብና እጅግ ላቂያ ያላቸውን ሐሳቦች ወደ ተግባር ለመለወጥ በመንቀሳቀስ ነው » ።
የአውሮፓው ኅብረት ፣ የመረጣቸው ፕሮጀክቶች፤ አንደኛ ፤ የሰውን ጭንቅላት ውስብስብና የረቀቀ አሠራር በህክምና ካርታ በጥልቅ በመመርመር ላይ ያተኮረ ነው።
ዓላማውም፤ የአእምሮ በሽታዎችን ከሥር ከመሠረቱ ለመቋቋም ፣ መጃጀትን ፣ መርሳትን ፤ እነዚህንና የመሳሰሉትን ማስወገድ የሚቻልበትን ብልሃት ለመሻት ነው ተብሏል።
ተክሌ የኋላ
ሂሩት መለሰ