1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኅብረቱ በኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንደሚያሳስበው ገልጿል

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 13 2010

የአውሮጳ ኅብረት የኢትዮጵያ መንግሥት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት ችግሮቹን በሰላማዊ መንገድ ይፈታ ዘንድ የሚያደርገውን ጥረት እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡ ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የኅብረቱ የውጭ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት ቃል አቃባይ ካትሬን ሬይ የህዝብ ጥያቄዎች ሊፈቱ የሚችሉት በሁሉ አቀፍ ውይይት ብቻ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

https://p.dw.com/p/2prJ3
Belgien EU-Parlament in Brüssel
ምስል picture-alliance/dpa/O. Hoslet

ኅብረቱ በኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንደሚያሳስበው ገልጿል

የአዉሮጳ ኅብረት ከትላንት በስቲያ ባወጡት መግለጫ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች እና በዩኒቨርስቲዎች እየታዩ ያሉት ሁከቶች እና ብሔር ተኮር ግጭቶች እንዳሳሰቡት ገልጿል፡፡ የክልልም ሆነ የፌዴራል የጸጥታ ኃይሎችም ከኃይል እርምጃ በመቆጠብ የዜጎቻቸውን ደህንነት እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡ የተፈጸሙትን ግድያዎች እና ወንጀሎች በገለልተኛ ወገን በማጣራት ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግም አሳስቧል፡፡ የብራስልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ የላከውን ዝርዝር ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። 

ገበያው ንጉሴ

ሸዋዬ ለገሠ