1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ህብረት እቅድና ኢጣልያ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 14 2007

ባለፈው ቅዳሜ ሌሊት በደረሰው የመርከብ መገልበጥና መስጠም አደጋ ከ800 የሚበልጡ ሰዎች ሕይወታቸውን ሳያጡ እንዳልቀረ ከተሰማ በኋላ የአውሮጳ ህብረት የውጭ እና የሀገር አስተዳደር ሚንስትሮች ከትናንት በስተያ

https://p.dw.com/p/1FCc2
Matteo Renzi im Parlament Italien
ምስል AFP/Getty Images/A. Solaro

በሉግዘምቡርግ ባካሄዱት ስብሰባ በነገው ዕለት በብራስልስ በሚካሄደው የህብረቱ መሪዎች በጉባዔ ላይ የሚቀርብ ባለ 10 ነጥቦች የድርጊት መርሀግብር ተቀብለዋል። ይህንኑ የጀልባ ስደተኞችን ለማዳን የሚያስችል እና ሕገ ወጥ ሰው አሸጋጋሪዎችን መረብ ማፈራረስ እንዲያስችል የወጣውን ባለ አስር ነጥብ እቅድ መሪዎቹ እንደሚያፀድቁት ይጠበቃል። ስለዚሁ የአውሮጳ ህብረት እቅድ ኢጣልያ ስላሰማችው አስተያየት የሮሙን ወኪላችን ተኽለእዝጊ ገብረየሱስን በስልክ አነጋግሬው ነበር።

ተኽለእዝጊ ገብረየሱስ

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ