1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውማ ኦባማ እና የአይ ዌይ አስተያየት

ሰኞ፣ ሚያዝያ 28 2005

« በመጀመሪያ ደረጃ እንኳን ለ 60 ኛው የምሥረታ ዓመት አደረሳችሁ። መልካም ልደት!! አንድ የውጭ ማሰራጪያ ጣቢያ በተለያየ ቋንቋ ማሠራጨቱ በጣም ግሩም ነው ብዬ አስባለሁ።

https://p.dw.com/p/18LMC
Die Deutsche Welle steht 2013 seit 60 Jahren im Dialog mit der Welt. Sendestart war der 3. Mai 1953. Artikelbild Amharisch
ምስል DW
Dr. Auma Obama, Kenier, Initiatorin und Vorsitzende der Jugendinitiative und Stiftung "SautiKuu - powerful Voices for a powerful youth" in Kenia. Sie ist die Halbschwester des US-Präsidenten Barack Obama, hat in Deutschland studiert (Heidelberg und Bayreuth) und in England gearbeitet, bevor sie nach Kenia zurückkehrte. Aufnahme: 27.11.2012, Bonn, Foto: Helle Jeppesen für DW
አውማ ኦባማምስል DW/ H. Jeppesen

ብዙ ባህሎችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በሚነሱበት ጊዜ ያካባቢው ቋንቋዎች እና ባህሎችም ግንዛቤ ውስጥ የሚገቡበት አሰራር ወሳኝ ነው። ይህ ትምህርት የሚቀሰምበት ሂደት ነው፤ በዚሁ ረገድ ዝግጅታችሁ በጣም ጥሩ ነው። ሥርጭታችሁ ከሕዝቦች ጋ በሚደረግ ውይይት ላይ የተመሠረተ፡ እነሱንም ያሳተፈ እና ለሀሳባቸውም ትኩረት የሰጠ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ። እና እንደማስበው ዶይቸ ቬለ ይህን እያደረገ ነው። መልካም ዕድል! »


ቻይናዊው አርቲስት አይ ዌይዌይ

ዶይቸ ቬለ ከተቋቋመ ዘንድሮ 60 ኛውን ዓመት ያከብራል። በነዚህ 60 ዓመታት ዶይቸ ቬለ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጠቃ ፖለቲካዊ እና ባህላዊ ሚና ተጫውቷል። በተለይ በቻይና የፕሬስ እና ሀሳብን የመግለጽ ነፃነትን ለማስፋፋት በተለይ የዶይች ቬለ የቻይና ቋንቋ ክፍል ከፍተኛ አገልግሎት አበርክቶዋል፤ ወደፊትም ከዚህ የበለጠ ሚና መጫወት እንደሚችል ተስፋ አደርጋለሁ።

Ausstellung PRIVAT
አርቲስት አይ ዌይዌይምስል Kunsthalle SCHIRN