1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

ዓርብ፣ ኅዳር 30 2009

የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን  ከነገ ጀምሮ ለአገር አቋራጭ አዉቶብሶች በቴክኖሎጅ የተደገፈ አዲስ የቲኬት ሽያጭ አገልግሎት እንደሚጀምር ለመረዳት ተችለዋል። ቀደም ሲል ትኬት ለማግኘት በቅድምያ የአዉቶቡስ መናሃርያ ሄዶ መግዛት ወይም አዛዉ እተሳፈሩበት አዉቶብስ ዉስጥ መቁረጥ እንደነበረ ይታወቃል። 

https://p.dw.com/p/2U2Hr
Deutschland Verkehr Lufthansa Streik ab Montag Pilot
ምስል AP

M M T/ Ethiopia New E-Ticketing for Buses - MP3-Stereo

«ኤሌክትሮኒክ ቲኬቲንግ» በመባል የሚታወቀዉ ይህ አገልግሎት ደንበኞች ቲኬቶችን ቀደም ብሎ በመግዛት «ግዜያቸዉን በአግባብ እንዲጠቀሙ» የሚያስችል፣ ትኬት ለማግኘት የሚያጋጥመዉን «እንግልትም» የሚያስቀር እና ከክፍያ ጋር ተያይዞው የሚመጡ ችግሮችን ለማስወገድ እንደታቀደ የባለስልጣኑ ሥራ አስኪያጅ አቶ ካሳሁን ኃይሌማርያም ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

ይህን አዲስ አገልግሎት ከማኅበረሰቡ ጋር ለማስተዋወቅ ፈተናዎች ሊገጥሙ እንደሚችልም አቶ ካሳሁን ጠቅሰዉ፤ በከፊልም አዲሱ አገልግሎት የተሽከርካሪ ባለንበረቶችን  ቅር ማሰኘቱ እንደማይቀር ይናገራሉ። በአዉቶብስ ተራ ዉስጥ በትኬት ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች በአዲሱ አገልግሎት ስረዓት ስለተጠቃለሉ ሥራቸዉን አይነጥቅም ለሚለዉ ይላሉ።

አዲሱ አገልግሎት ነገ በአዲስ አበባ ዉስጥ ያሉት አምስቱም መነሃርያዎች እንደሚጀመር የሚናገሩት አቶ ካሳሁን ከ15 ቀን በኋላ በመድናይቱ ዉስጥ ያሉት 65 የትኬት ወኪሎች ይህን አገልግሎት መስጠት እንደሚጀሚሩም ያብራራሉ። ከአንድ ወር በኋላ ደግሞ «ለሁሉም» የተሰኘዉ 34 የመብራት፣ የዉኃና የስልክ ክፍያ የሚፈፀሚባቸዉ ጣብያዎች  ሄዶ «ኤሌክትሮንክ ቲኬት» መግዛት እንደሚቻልም ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

አሄን ጉዳይ በተመለከተ በፌስቡክ ደህረ ገፃችን ላይ አወያይተን ነበር። አስተያየታቸዉን ካጋሩን ዉስጥም በነበርዉ አሰራር «ብዙ ችግሮች» ስደርሱ እንነበር ጠቅሶ አድሱ አገልግሎት «ህዝቡን ሌልት ከሌባ እና ከብርድ ይታደጋል» ይላሉ። በሌላ በሁኩሊም ይህ አገልጊሎት በትራንስፖርት ብቻ ሳይሆን «በሆቴል፣ በጉብኝት፣ በኢንተርቴይመንት መስኮች መስፋፋት አለበት» ካሉ በዋላ «ይህ ማሽን በቂና ፈጣን የኢንተርኔት [ኔትዎርክ] ይፈልጋል፣ አለበለዚያ ማቀዝቀዣው የማይሰራ ፍሪጅ ነው የሚሆነው» ስሉ አስተያየታቸዉን አጋርቶናል።

መርጋ ዮናስ

አረያም ተክሌ