1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጻዉ ህብረት የባህል አጀንዳ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 1 2000

የሼክስፒር የትያትር ድርሰት፣ የማክሲም ጎርኪ የፑሽኪ ስነጹሁፍ የጀርመኑ ጎይተ የግጥም ስራ፣ የቫንጎግ የስዕል ስራ ፣ የሉችያኖ ፓቫሮቲ ኦጼራ፣ አዉሮጻን ከሚያስጠሩት ከያንያን እና ጠቢባን መካከል ጥቂቶቹ የጥበብ ቱሩፋቶች ናቸዉ። በያዝነዉ ሳምንት በአዉሮጻ የሚኖረዉን ህዝብ ይበልጥ በአንድ ጥላ ለማሰባሰብ በሚል፣ የአዉሮጻዉ ህብረት፣ መጭዉ የአዉሮጻዉያኑ አመት በአህጉሪቱ ዉስጥ በሚኖረዉ ህዝብ መካከል ያለዉን የተለያየ አገረሰባዊ ልማድ፣ እምነት፣ በ

https://p.dw.com/p/E0lx
ምስል AP

�ለከተ ህዝብ የዉይይት መድረክ እንዲከፍት ወስኖአል

በመሆኑም መጭዉ የአዉሮፓዉያኑ 2008 አ.ም፣ አዉሮጻ በባህል ዙርያ ዉይይት የሚያደርግበት አመት ተብሎ እንዲሰየም ዉሳኔ ተላልፎአል። ህብረቱ ባህልን ለማስተዋወቅ እቅዱ ምን ይሆን? ዛሪ የባህል መድረካችን የምንቃኘዉ ርእስ ይሆናል፣ ሌላዉ ለአዉሮጻ ምርጥ የፊልም ስራ በበርሊን የሽልማት ስነ-ሰስርአት፣ እንዲሁም በዲስልዶርፍ 1300 የአለም ምርጥ የፊልም አክተሮች የተካፈሉበት ስለ ጀርመኑ ተደናቂ የፊልም ስራ ሽልማት ያስቃኘናል።