1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጻዉ ህብረት እና የሜዲተራንያን ባህር አዋሳኝ አገሮች ህብረት

ሐሙስ፣ ሐምሌ 9 2001

የፈረንሳዩ ፕሪዝደንት ኒኮላ ሳርኮዚ የአዉሮጻዉ ህብረት የምክር ቤት ፕሪዝደንት ስልጣን ላይ ሳሉ የሜዲተራንያን ባህር አዋሳኝ አገሮች ህብረት በተሰኘ ፓሪስ ላይ የመሰረቱት የአገሮች ህብረት አንድ አመትን አስቆጥሮአል።

https://p.dw.com/p/Ir3P
የሜዲተራንያን ባህር አዋሳኝ አገሮች ህብረት መንግስታት በብረስልስ ስብሳባ በኻላምስል AP

በሜዲተርንያን ባህር ዙርያ ያሉ አገሮች እና የአዉሮጻዉ ህብረት በጋራ እንዲሰሩ እንዲያስችል ሳርኮዚ በስልጣናቸዉ ዘመን ያቋቋሞት ህብረት በግዜዉ ጀርመን የህብረቱን መቋቋም አለመፈለግዋን ብታሳይም ከብዙ ክርክር እና ጭቅጭቅ በኻላ በሜዲተራንያን ዙርያ ያሉ አገሮችን እና የአዉሮጻዉን ህብረት ያካተተ ህብረት ተቋቋመ። ብዙ እቅዶችን ይዞ የተመሰረተዉ ይህ ማህበር ከአንድ አመት በኻላ ያሳየዉ እድገት እና ዉጤት አጥጋቢ ሆኖ አልተገኘም። በተለይ በሞሮኮ ዉስጥ ከፍተኛ ቅሪታን አስነስቶአል። ያም ሆነ ይህ ማህበሩ ወደፊት አጥጋቢ ዉጤትን ያሳያል በሚል ተስፋ አልተቆረጠም። የዶቸ ቬለዉ Davina Weitowitz የዘገበዉን አዜብ ታደሰ እንዲህ አጠናቅራዋለች


የሜዲተራንያን ባህር አዋሳኝ አገሮች እና የአዉሮጻዉ ህብረት የጋራ የትብብር ስራ ምን ያህል ስኬታማ ነዉ በሚል ስለ ህብረቱ አፍሪቃዉያን እንብዛም ጠርንካራ አስተያየት የላቸዉም። ከአዉሮጻዉ ህብረት አገሮች ጋራ የትብብር ስራ እንዲሰሩ ለማስቻል የዛሪ አመት ፓሪስ ላይ 43 አገራት ካቋቋሙት ማህበር ቀደም ብሎ እንደ አዉሮጻዉያኑ 1995 አ.ም የተቋቋመዉ የ Barcelona Prosess የተሰኘዉ ህብረት ተቋቁሞ ነበር። የሜዲተራንያን አዋሳኝ አገሮች ህብረት የተሰኘዉ ማህበር ከተቋቋመ አንድ አመት በኻላ የማህበሩ አባል አገራት ማህበሩ ይፈጽማል ያላቸዉን ድርጊቶች ዳር ባለማድረሱ ቅሪታቸዉን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ። የሞሮኮ ባለስልጣናትም የሜዲተራንያን ባህር አዋሳኝ አገሮች ማህበር ለአባል አገራቱ ምን እየፈጸመ ነዉ ሲሉ ጥያቄያቸዉን አንስተዋል።
ሊሰራ የታቀደዉ ሞሪታንያን ሞሮኮን አልጀርያን ቱኒዝያን እንዲሁም ሊቢያን የሚያቋርጠዉ ሶስት ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀት ያለዉ አዉራ ጎዳና፣ ተፈጥሮአዊ አደጋዎችን በአካባቢዉ አገራት ለመቋቋም እንዲሁም የሜዲተራንያን ባህር ንጽህናን ለመጠበቅ የተሰኙት መረሃግብሮች ማህበሩ ሲቋቋም ሊተገበሩ የታቀዱ ናቸዉ። ነገር ግን ማህበሩ ከተቋቋመ ከአንድ አመት በኻላ ያሳየዉ ተጨባጭ ተግባር አይታይም። በሞሮኮ የንጉስ አማካሪ የሆኑት Andre Azoulay ትግስት! ትግስት ይኑረን ሲሉ ይገልጻሉ።

«በሜዲተራንያን ባህር አዋሳኝ በሰሜንም ሆነ በደቡብ የሚገኙ አገሮች በማህበሩ ድጋፍ ከነገ ዛሪ በአፋጣኝ አንድ ነገር ይሰራል ብዪ አልሜም አላዉቅም። እንደ መናም ከሰማይ ማዉረድ አይችልም። ማህበሩ በርካታ ችግሮች ሲያጋጥሙት ግን የማህበሩ መቋቋም አስፈላጊነት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ነዉ የሚያረጋግጥልኝ»
ከአንድ አመት በፊት Andre Azoulay በሰጡት ቃለ ምልልስ የሜዲተራንያን ባህር አዋሳኝ አገሮች ህብረት በፊልስጤም እና እስራኤል መካከል ያለዉን ዉጥረት ለመፈታት አንድ ቁልፍ ሊሆን ይችላል ሲሉ መግለጻቸዉ ቢታወስም ማህበሩ በጋዛ ሰርጥ ያለዉን ጦርነት ለመፍታት ምንም አይነት ጥረት ሲያደርግ አልታየም። የሜዲተራንያን ባህር አዋሳኝ አገሮች ማህበር የተቀናጀ ስራ ለመተግበር ገና ቢቀረዉም ተስፋ የሚጣልበት መሆኑን የሞሮኮዉ ንጉስ አማካሪ Andre Azoulay ይገልጻሉ።

«ማህበሩ በፖለቲካ እና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ወደ ኻላ የተጎተተ ተሳትፎ ነዉ ያለዉ ቢሆንም ቅሉ ለምሳሌ ግብጽ አሌክሳንድርያ ላይ በቅርቡ የማህበሩ አባል አገራት ስብሰባ አድርገዉ ነበር። በዚሁ ስብሰባቸዉ ላይ ለማህበሩ አባል አገራት ለመሰረተ ልማት ወጪ እንዲዉል ግማሽ ቢሊዮን ዶላልር ወጪ እንዲሆን ወስኖአል»
በቅርቡ አልጀርያ የህብረቱ አባል አገር እንደሆነች እንደገና አሳዉቃለች። ከቱኒዝያ ደግሞ ብዙም አይሰማም ምንም እንኻ ለማህበሩ ያላትን በሮች ሁሉ ከፍታ ብትገኝም። ከሞሮኮ ግን ስለማህበሩ ትችት ይሰማል። በሞሮኮ የአለማቀፍ ግንኙነት ተቋም ፕሪዝደንት የሆኑት Jawad Kerdoudi ማህበሩ ሜዲተራንያን ባህርን ለሚያዋስኑ አገሮች አደርጋለሁ በሚለዉ እንቅስቃሴ ጥርጥር አላቸዉ
«በአንድነት ምንም አይነት የጋራ አላማን ሳይዝ የተመሰረተ ህብረት ነዉ። 43 አገራትን ያካተተዉ ማህበር በካርታ ወሰን ላይ አንድ ይሁኑ እንጂ በአላማዉ አንድ ያልሆነ ማህበር ነዉ። ሌላዉ ማህበሩ ስም እንደሚገልጸዉ በሜዲተራንያን ባህር ወሰን ላይ የሚገኙ ናቸዉ። ግን አንዳንዶች የአዉሮጻዉ ህብረት አባል አገራት ሜዲተራንያን ባህር አያዋስናቸዉም። ሌላዉ ልዩነት ደግሞ ደሃ እና ባለጸጋ ፣ የተለያየ ባህል እና ሃይማኖትን ያላቸዉን አገሮችንም ነዉ ያካተተዉ። ስለዚህም ማህበሩ እዉነተኛ የተሳካለት ህብረት ይሆናል የሚል እምነት የለኝም»
ምንም እንኻ ማህበሩ ትችት ቢደርስበትም ከተቋቋመ አንድ አመት ሊሞላዉ ሲል የማህበሩ አባል አገራት ፓሪስ እና ብረስልስ ላይ በመሰባሰብ ህብረቱ ጭራሽ አለመሞቱን አስመስክረዋል። Schwaya Schwaya ያሉት የሞሮኮ ተወላጆች በቋንቋቸዉ ቀስ በቀስ በማለት፣ማህበሩ አንደኛ አመቱን ሲያስብ በትችት ያስተጋቡት ቢሆንም ቅሉ ማህበሩ ቀስ በቀስ የጀመረዉን ምግባሩን ቶሎ ቶሎ ብሎ ዉጤት ላይ እንደሚደርስ ተስፋ ያደርጋሉ።

አዜብ ታደሰ፣ ሸዋዩ ለገሰ፣ አርያም ተክሌ