የአዉሮጳ ፊልም ፊስቲቫል በአዲስ አበባ
ሐሙስ፣ ሰኔ 13 2005ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ በሚገኙ አራት የአዉሮጳ አገራት የባህል ተቋማት ዉስጥ፤ ግንቦት 26 የጀመረዉ፤የአዉሮጳ የፊልም ፊስቲቫል፤ እስከ ፊታችን ሰኞ ሰኔ 10 ድረስ ይቀጥላል። በዚህ ፊስቲቫል የተለያዩ የአዉሮጳ ሀገር ፊልሞች ከመታየታቸዉም በላይ፤ የተለያዩ አዉደ ጥናቶችም በመደረግ ላይ ናቸዉ። ፊልም ምስል ብቻ ሀገርን ባህልን ማንነትን እና ፍላጎትን በቀላል ማስተዋወቅ የሚችል፤ ታላቅ መሳርያ በመሆኑ በሀገራችን ለፊልም ሥራ እድገት የሚደረገዉ ድጋፍ መጠንከር እና መበረታታት አለበት ያሉንን በለቱ ቅንብራችን ቃለ ምልልስ የሰጡን ተሳታፊዎች በሙሉ በዶቼ ቬለ ሥም እናመሰግናለን። ያድምጡ!
አዜብ ታደሰ