የአዉሮጳ ጥምር ጦር ምሥረታ እቅድ
ማክሰኞ፣ መጋቢት 1 2007ማስታወቂያ
ዩንከር «ዲ ቬልት » ለተሰኘዉ ጋዜጣ ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ እንደገለፁት የሚመሰረተዉ ጥምር ጦር፤ ወድያዉ ለስምሪት የሚላክ ስይሆን፤ ለጋራና ደሕንነቱ ለተጠበቀ አዉሮጳ የዉስጥና የዉጭ ፖለቲካ የሚቆም፤ አዉሮጳ በዓለም ያላትን ኃላፊነት የሚያረጋገጥ ነዉ ብለዋል። የጀርመንዋ መከላከያ ሚኒስትር ኡርዙላ ፎን ደርላየን የዩንከርን ሐሳብ ሲደግፉ፤ እንግሊዝን ጨምሮ በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ ፖለቲከኞች ሃሳቡን በጥርጣሪ ነዉ የተመለከቱት። በዚህ ዝግጅታችን የአውሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ዛን ክሎድ ዩንከር አዉሮጳ አቀፍ ጥምር ጦር ምሥረታ እቅድን በተመለከተ የዶይቼ ቬለዉ ሲቨን ፖይለ ያቀረበዉን ዘገባ ይዘን ብራስልስ የሚገኘዉን ወኪላችንን ገበያዉ ንጉሴን አነጋግረን ቅንብር ይዘናል።